ኢሳይያስ 42:1-25

  • የአምላክ አገልጋይ የተሰጠው ተልእኮ (1-9)

    • ‘ስሜ ይሖዋ ነው’ (8)

  • ለይሖዋ የቀረበ አዲስ የውዳሴ መዝሙር (10-17)

  • እስራኤል ዕውርና ደንቆሮ ነው (18-25)

42  እነሆ፣ ደግፌ የያዝኩት፣ ደስ የምሰኝበትና*+ የመረጥኩት+ አገልጋዬ!+ መንፈሴን በእሱ ላይ አድርጌአለሁ፤+እሱ ለብሔራት ፍትሕን ያመጣል።+   አይጮኽም ወይም ድምፁን ከፍ አያደርግም፤ድምፁንም በጎዳና ላይ አያሰማም።+   የተቀጠቀጠን ሸምበቆ አይሰብርም፤የሚጨስንም የጧፍ ክር አያጠፋም።+ ፍትሕን በታማኝነት ያመጣል።+   እሱ ፍትሕን በምድር ላይ እስኪያሰፍን ድረስ አይሰበርም ወይም ብርሃኑ አይደክምም፤+ደሴቶችም ሕጉን* በተስፋ ይጠባበቃሉ።   ሰማያትን የፈጠረውና የዘረጋው፣+ምድርንና በውስጧ ያሉትን ነገሮች ሁሉ የሠራው፣+በላይዋም ለሚኖሩ ሰዎች እስትንፋስን፣+በእሷም ላይ ለሚመላለሱ መንፈስን የሰጠው+እውነተኛው አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦   “እኔ ይሖዋ በጽድቅ ጠርቼሃለሁ፤እጅህን ይዣለሁ። እጠብቅሃለሁ፤ እንዲሁም ለሰዎች ቃል ኪዳን፣ለብሔራትም ብርሃን አድርጌ እሰጥሃለሁ፤+   አንተም የዓይነ ስውራንን ዓይን ታበራለህ፤+እስረኛውን ከወህኒ ቤት፣በጨለማ ውስጥ የተቀመጡትንም ከእስር ቤት ታወጣለህ።+   እኔ ይሖዋ ነኝ። ስሜ ይህ ነው፤ክብሬን ለሌላ፣*ምስጋናዬንም ለተቀረጹ ምስሎች አልሰጥም።+   እነሆ፣ የቀደሙት ነገሮች ተፈጽመዋል፤አሁን ደግሞ አዳዲስ ነገሮችን እናገራለሁ። ገና ከመከሰታቸው በፊት ስለ እነሱ እነግራችኋለሁ።”+ 10  እናንተ በባሕር ላይና በውስጡ ባሉት ፍጥረታት መካከል የምትጓዙ፣እናንተ ደሴቶችና በእነሱ ላይ የምትኖሩ ሁሉ፣+ለይሖዋ አዲስ መዝሙር ዘምሩ፤+ከምድር ዳርቻም ውዳሴውን አሰሙ።+ 11  ምድረ በዳውና በዚያ ያሉ ከተሞች፣ቄዳር+ ያለችባቸውም ሰፈሮች ድምፃቸውን ከፍ ያድርጉ።+ ዓለታማ በሆኑ ቦታዎች የሚኖሩ ሰዎች በደስታ እልል ይበሉ፤በተራሮችም አናት ላይ ሆነው ይጩኹ። 12  ለይሖዋ ክብር ይስጡ፤በደሴቶችም ላይ ውዳሴውን ያውጁ።+ 13  ይሖዋ እንደ ኃያል ሰው ይወጣል።+ እንደ ተዋጊ ቅንዓቱን ይቀሰቅሳል።+ ይጮኻል፤ አዎ፣ ቀረርቶ ያሰማል፤ከጠላቶቹ ይበልጥ ኃያል መሆኑን ያሳያል።+ 14  “ለረጅም ጊዜ ዝም አልኩ። ጸጥ ብዬ ቆየሁ፤ ራሴንም ገታሁ። ምጥ እንደያዛት ሴትእቃትታለሁ፣ አለከልካለሁ እንዲሁም ቁና ቁና እተነፍሳለሁ። 15  ተራሮችንና ኮረብቶችን አወድማለሁ፤ደግሞም በላያቸው ላይ ያለውን ተክል ሁሉ አደርቃለሁ። ወንዞችን ደሴቶች* አደርጋለሁ፤ቄጠማ የሞላባቸውንም ኩሬዎች አደርቃለሁ።+ 16  ዓይነ ስውራንን በማያውቁት መንገድ እመራቸዋለሁ፤+ባልለመዱት ጎዳናም እንዲሄዱ አደርጋቸዋለሁ።+ ጨለማውን በፊታቸው ብርሃን፣+ወጣ ገባ የሆነውንም ምድር ደልዳላ ሜዳ አደርጋለሁ።+ ይህን አደርግላቸዋለሁ፤ ደግሞም አልተዋቸውም።” 17  በተቀረጸ ምስል የሚታመኑ፣ከብረት የተሠሩትን ሐውልቶች* “እናንተ አምላኮቻችን ናችሁ” የሚሉወደ ኋላ ይመለሳሉ፤ እጅግም ያፍራሉ።+ 18  እናንተ ደንቆሮዎች፣ ስሙ፤እናንተ ዕውሮች እዩ፤ ተመልከቱም።+ 19  ከአገልጋዬ በቀር የታወረ፣እንደምልከው መልእክተኛዬም ደንቆሮ የሆነ ማን አለ? ብድራት እንደተከፈለው ሰው ዕውር የሆነወይም እንደ ይሖዋ አገልጋይ የታወረ ማን ነው?+ 20  ብዙ ነገሮች ብታዩም ልብ የምትሉት ነገር የለም። ጆሮዎቻችሁን ብትከፍቱም ምንም አትሰሙም።+ 21  ይሖዋ ለጽድቁ ሲልሕጉን* ታላቅና ክብራማ በማድረግ ደስ ተሰኝቷል። 22  ይህ ሕዝብ ግን የተበዘበዘና የተዘረፈ ነው፤+ሁሉም ጉድጓድ ውስጥ ተይዘዋል፤ በእስር ቤትም ተሰውረዋል።+ የሚታደጋቸው በሌለበት ተበዝብዘዋል፤+“መልሷቸው!” የሚል በሌለበትም ተዘርፈዋል። 23  ከእናንተ መካከል ይህን የሚሰማ ማን ነው? በትኩረት የሚያዳምጥና ለወደፊቱ ጊዜ ትምህርት የሚወስድ ማን ነው? 24  ያዕቆብን ለዘረፋ፣እስራኤልንም ለበዝባዦች አሳልፎ የሰጠ ማን ነው? በእሱ ላይ ኃጢአት በመፈጸም የበደልነው ይሖዋ አይደለም? እነሱ በመንገዱ ለመሄድ አልፈለጉም፤ሕጉንም* አይታዘዙም።+ 25  ስለዚህ ንዴቱን፣ ቁጣውንና የጦርነቱን መዓትበእስራኤል ላይ አፈሰሰ።+ የጦርነቱም እሳት በዙሪያው ያለውን ሁሉ በላው፤ እሱ ግን አላስተዋለም።+ አቃጠለው፤ እሱ ግን ጨርሶ ልብ አላለም።+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ነፍሴ ደስ የምትሰኝበትና።”
ወይም “መመሪያውን፤ ትምህርቱን።”
ወይም “ክብሬን ለማንም አላጋራም።”
ወይም “በባሕር አጠገብ ያለ መሬት።”
ወይም “ቀልጠው የተሠሩትን ሐውልቶች።”
ወይም “መመሪያውን፤ ትምህርቱን።”
ወይም “መመሪያውንም፤ ትምህርቱንም።”