በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ


የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ከአስተማሪ ጋር

ለዘላለም በደስታ ኑር!

ያለክፍያ የምንሰጠው ይህ አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት፣ ለጥያቄዎችህ መልስ ይሰጥሃል፤ ለምሳሌ፦

  • በሕይወቴ ደስተኛ መሆን የምችለው እንዴት ነው?

  • ችግር እና መከራ የማይኖርበት ጊዜ ይመጣ ይሆን?

  • በሞት ያጣኋቸውን ቤተሰቦቼንና ወዳጆቼን እንደገና አገኛቸዋለሁ?

  • አምላክ የእኔ ጉዳይ ያሳስበዋል?

  • አምላክ ጸሎቴን የሚሰማው እንዴት አድርጌ ብጸልይ ነው?

በነፃ ነው

ሙሉው ትምህርት የሚሰጠው ያለክፍያ ነው፤ ለዘላለም በደስታ ኑር! የተባለውን መማሪያ መጽሐፍ እና ከፈለግህ መጽሐፍ ቅዱስም በነፃ መውሰድ ትችላለህ።

ምቹ ነው

ከአስተማሪህ ጋር ከፈለግህ በአካል ወይም በስልክና በኢንተርኔት መገናኘት ትችላላችሁ፤ በፈለግከው ሰዓት፣ በፈለግከው ቦታ።

በፈቃደኝነት ነው

በፈለግከው ጊዜ ትምህርቱን ማቋረጥ ትችላለህ፤ ምንም ግዴታ ውስጥ የሚያስገባህ ነገር የለም።

ትምህርቱ የሚሰጠው እንዴት ነው?

በግልህ አንድ አስተማሪ ይመደብልሃል፤ እሱም መጽሐፍ ቅዱስን ርዕስ በርዕስ ያስተምርሃል። ለዘላለም በደስታ ኑር! በተባለው አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ ኮርሳችን አማካኝነት፣ መጽሐፍ ቅዱስ ምን መልእክት እንደያዘ እንዲሁም አንተን እንዴት እንደሚጠቅምህ ደረጃ በደረጃ ትማራለህ። ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ቪዲዮ ተመልከት፤ ወይም ይህን ኮርስ አስመልክቶ ብዙ ጊዜ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምን ብለን መልስ እንደሰጠን አንብብ።

መማሪያ መጽሐፉ ምን እንደሚመስል ማየት ትፈልጋለህ?

የመጽሐፉን የመጀመሪያ ምዕራፎች እናስቃኝህ።

ለምን አትሞክረውም?

የመጽሐፍ ቅዱስ ኮርሱ እንዲጀመርልህ ፕሮግራም ለማስያዝ ከታች ያለውን ሊንክ ጠቅ አድርግ።