በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ጥያቄ 15

ደስተኛ መሆን የምትችለው እንዴት ነው?

 “ጥላቻ ባለበት የሰባ ፍሪዳ ከመብላት ይልቅ ፍቅር ባለበት አትክልት መብላት ይሻላል።”

ምሳሌ 15:17

 “የሚጠቅምህን ነገር የማስተምርህ፣ ልትሄድበትም በሚገባህ መንገድ የምመራህ እኔ ይሖዋ አምላክህ ነኝ።”

ኢሳይያስ 48:17

 “መንፈሳዊ ነገሮችን የተጠሙ ደስተኞች ናቸው፤ መንግሥተ ሰማያት የእነሱ ነውና።”

ማቴዎስ 5:3

 “ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ።”

ማቴዎስ 22:39

 “ልክ ሰዎች እንዲያደርጉላችሁ እንደምትፈልጉት ሁሉ እናንተም እንዲሁ አድርጉላቸው።”

ሉቃስ 6:31

 “ደስተኞችስ የአምላክን ቃል ሰምተው የሚጠብቁት ናቸው!”

ሉቃስ 11:28

 “አንድ ሰው ሀብታም ቢሆንም እንኳ ንብረቱ ሕይወት ሊያስገኝለት አይችልም።”

ሉቃስ 12:15

 “ስለዚህ ምግብና ልብስ ካለን በእነዚህ ነገሮች ረክተን መኖር ይገባናል።”

1 ጢሞቴዎስ 6:8

 “ከመቀበል ይልቅ መስጠት የበለጠ ደስታ ያስገኛል።”

የሐዋርያት ሥራ 20:35