በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከአምላክ ቃል ጋር ተዋወቅ

መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክን መልእክት ወይም ቃል ይዟል። ሕይወታችንን በተሳካ መንገድ መምራት የምንችለው እንዴት እንደሆነና በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘት ምን ማድረግ እንዳለብን ይነግረናል። ከዚህም በተጨማሪ ለሚከተሉት ጥያቄዎች መልስ ይዟል፦

 1. 1 አምላክ ማን ነው?

 2. 2 ስለ አምላክ ማወቅ የምትችለው እንዴት ነው?

 3. 3 መጽሐፍ ቅዱስን የጻፈው ማን ነው?

 4. 4 መጽሐፍ ቅዱስ ከሳይንስ አንጻር ትክክል ነው?

 5. 5 የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት ምንድን ነው?

 6. 6 መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መሲሑ ምን ትንቢት ተናግሯል?

 7. 7 መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ዘመናችን ምን ትንቢት ተናግሯል?

 8. 8 በሰዎች ላይ ለሚደርሰው መከራና ሥቃይ ተጠያቂው አምላክ ነው?

 9. 9 ሰዎች መከራና ሥቃይ የሚደርስባቸው ለምንድን ነው?

 10. 10 መጽሐፍ ቅዱስ የወደፊቱን ጊዜ በተመለከተ ምን ተስፋ ይዟል?

 11. 11 ሰው ሲሞት ምን ይሆናል?

 12. 12 በሞት ያጣናቸውን ሰዎች በተመለከተ ምን ተስፋ አለን?

 13. 13 መጽሐፍ ቅዱስ ሥራን አስመልክቶ ምን ይላል?

 14. 14 ያሉህን ነገሮች በጥበብ መጠቀም የምትችለው እንዴት ነው?

 15. 15 ደስተኛ መሆን የምትችለው እንዴት ነው?

 16. 16 ጭንቀትን መቋቋም የምትችለው እንዴት ነው?

 17. 17 መጽሐፍ ቅዱስ ለቤተሰብህ ሕይወት ጠቃሚ ሊሆን የሚችለው እንዴት ነው?

 18. 18 ወደ አምላክ መቅረብ የምትችለው እንዴት ነው?

 19. 19 በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙት መጻሕፍት ምን ይዘዋል?

 20. 20 ከመጽሐፍ ቅዱስ ንባብህ የተሻለ ጥቅም ማግኘት የምትችለው እንዴት ነው?

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ማውጣት የሚቻልበት ዘዴ

መጽሐፍ ቅዱስ 66 ትናንሽ መጻሕፍትን የያዘ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ በሁለት የሚከፈል ሲሆን አንደኛው የዕብራይስጥና የአረማይክ ቅዱሳን መጻሕፍት (“ብሉይ ኪዳን”)፣ ሌላኛው ደግሞ የግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት (“አዲስ ኪዳን”) በመባል ይታወቃል። እያንዳንዱ የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ በምዕራፎችና በቁጥሮች የተከፋፈለ ነው። ጥቅሶች በሚጠቀሱበት ጊዜ ከመጽሐፉ ስም ቀጥሎ የሚገኘው የመጀመሪያው ቁጥር የመጽሐፉን ምዕራፍ የሚያመለክት ሲሆን ቀጥሎ ያለው አኃዝ ደግሞ ሐሳቡ የሚገኝበትን ቁጥር የሚጠቁም ነው። ለምሳሌ ያህል፣ ዘፍጥረት 1:1 ሲባል ዘፍጥረት ምዕራፍ 1 ቁጥር 1 ማለት ነው።