መዝሙር 76:1-12

  • አምላክ በጽዮን ጠላቶች ላይ የተቀዳጀው ድል

    • አምላክ የዋሆችን ያድናል (9)

    • ኩሩ የሆኑ ጠላቶች ይዋረዳሉ (12)

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ በባለ አውታር መሣሪያዎች የሚታጀብ። የአሳፍ+ ማህሌት። መዝሙር። 76  አምላክ በይሁዳ የታወቀ ነው፤+ስሙም በእስራኤል ታላቅ ነው።+   መጠለያው በሳሌም+ ነው፤መኖሪያውም በጽዮን ነው።+   በዚያም የሚንበለበሉትን ፍላጻዎች፣ጋሻን፣ ሰይፍንና የጦር መሣሪያዎችን ሰባበረ።+ (ሴላ)   አንተ ደምቀህ ታበራለህ፤*አዳኝ አራዊት ከሚኖሩባቸው ተራሮች ይልቅ ታላቅ ግርማ ተጎናጽፈሃል።   ልበ ሙሉ የሆኑት ሰዎች ተዘርፈዋል።+ እንቅልፍ ጥሏቸዋል፤ተዋጊዎቹ በሙሉ መከላከል የሚችሉበት ኃይል አልነበራቸውም።+   የያዕቆብ አምላክ ሆይ፣ ከተግሣጽህ የተነሳባለ ሠረገላውም ሆነ ፈረሱ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ወስዷቸዋል።+   አንተ ብቻ እጅግ የምትፈራ ነህ።+ ኃይለኛ ቁጣህን ማን ሊቋቋም ይችላል?+   አንተ ከሰማይ ፍርድ ተናገርክ፤+ምድር ፈርታ ዝም አለች፤+   ይህም የሆነው አምላክ በምድር ላይ የሚኖሩትን የዋሆች ሁሉ ለማዳን+ፍርድ ሊያስፈጽም በተነሳበት ጊዜ ነው። (ሴላ) 10  የሰው ቁጣ ለአንተ ውዳሴ ያመጣልና፤+በቀረው ቁጣቸው ራስህን ታስጌጣለህ። 11  ለአምላካችሁ ለይሖዋ ተሳሉ፤ ስእለታችሁንም ፈጽሙ፤+በዙሪያው ያሉ ሁሉ በፍርሃት ስጦታቸውን ያምጡ።+ 12  እሱ የመሪዎችን ኩራት* ያስወግዳል፤በምድር ነገሥታት ላይ ፍርሃት ያሳድራል።

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “አንተ ብርሃን ተላብሰሃል።”
ቃል በቃል “መንፈስ።”