መዝሙር 130:1-8

  • “ከጥልቅ ውስጥ አንተን እጣራለሁ”

    • “አንተ ስህተትን የምትከታተል ቢሆን ኖሮ” (3)

    • በይሖዋ ዘንድ ይቅርታ አለ (4)

    • “ይሖዋን በጉጉት እጠባበቃለሁ” (6)

ወደ ላይ የመውጣት መዝሙር። 130  ይሖዋ ሆይ፣ ከጥልቅ ውስጥ አንተን እጣራለሁ።+   ይሖዋ ሆይ፣ ድምፄን ስማ። ጆሮዎችህ እርዳታ ለማግኘት የማቀርበውን ልመና በትኩረት ያዳምጡ።   ያህ* ሆይ፣ አንተ ስህተትን የምትከታተል* ቢሆን ኖሮ፣ይሖዋ ሆይ፣ ማን ሊቆም ይችል ነበር?+   በአንተ ዘንድ በእርግጥ ይቅርታ አለና፤+ይህም ሰዎች አንተን እንዲፈሩ* ያደርጋል።+   ይሖዋን ተስፋ አደርጋለሁ፤ ሁለንተናዬ በእሱ ተስፋ ያደርጋል፤*ቃሉን በትዕግሥት እጠብቃለሁ።   ንጋትን ከሚጠባበቁ፣አዎ፣ ንጋትን ከሚጠባበቁ ጠባቂዎች ይበልጥይሖዋን በጉጉት እጠባበቃለሁ።*+   እስራኤል ይሖዋን በትዕግሥት ይጠባበቅ፤ይሖዋ በፍቅሩ ታማኝ ነውና፤+ሕዝቡንም ለመዋጀት ታላቅ ኃይል አለው።   እስራኤልን ከበደላቸው ሁሉ ይዋጃል።

የግርጌ ማስታወሻዎች

“ያህ” የይሖዋ ስም አጭር መጠሪያ ነው።
ወይም “በትኩረት የምትመለከት።”
ወይም “ለአንተ አክብሮታዊ ፍርሃት እንዲያድርባቸው።”
ወይም “ነፍሴ በእሱ ተስፋ ታደርጋለች።”
ወይም “ነፍሴ ይሖዋን በጉጉት ትጠባበቃለች።”