መዝሙር 138:1-8

  • አምላክ ከፍ ያለ ቢሆንም ያስብልናል

    • ‘ጸሎቴን መለስክልኝ’ (3)

    • ‘በአደጋ መካከል እንኳ ሕይወቴን ትጠብቃለህ’ (7)

የዳዊት መዝሙር። 138  በሙሉ ልቤ አወድስሃለሁ።+ በሌሎች አማልክት ፊትየውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ።*   ከታማኝ ፍቅርህና ከታማኝነትህ የተነሳወደ ቅዱስ መቅደስህ እሰግዳለሁ፤+ስምህንም አወድሳለሁ።+ ቃልህና ስምህ ከሁሉም ነገር በላይ ጎልቶ እንዲታይ አድርገሃልና።*   በተጣራሁ ቀን መለስክልኝ፤+ደፋርና* ብርቱ አደረግከኝ።+   ይሖዋ ሆይ፣ የምድር ነገሥታት ሁሉ ያወድሱሃል፤+የተናገርካቸውን የተስፋ ቃሎች ይሰማሉና።   ስለ ይሖዋ መንገዶች ይዘምራሉ፤የይሖዋ ክብር ታላቅ ነውና።+   ይሖዋ ከፍ ያለ ቢሆንም ትሑት የሆነውን ሰው ይመለከታል፤+ትዕቢተኛውን ግን ወደ እሱ እንዲቀርብ አይፈቅድም።+   አደገኛ በሆነ አካባቢ ባልፍም እንኳ አንተ ሕይወቴን ትጠብቃለህ።+ በጠላቶቼ ቁጣ ላይ እጅህን ትዘረጋለህ፤ቀኝ እጅህ ያድነኛል።   ይሖዋ ለእኔ ሲል ሁሉንም ነገር ይፈጽማል። ይሖዋ ሆይ፣ ታማኝ ፍቅርህ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል፤+የእጅህን ሥራ ቸል አትበል።+

የግርጌ ማስታወሻዎች

“ሌሎች አማልክትን በመቃወም ለአንተ ዜማ አሰማለሁ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
“ከስምህ ሁሉ በላይ ቃልህ ጎልቶ እንዲታይ አድርገሃል” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “በነፍሴ ደፋርና።”