መዝሙር 61:1-8

  • አምላክ ከጠላት የሚጠብቅ ጽኑ ግንብ ነው

    • ‘በድንኳንህ በእንግድነት እቀመጣለሁ’ (4)

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ በባለ አውታር መሣሪያዎች የሚታጀብ። የዳዊት መዝሙር። 61  አምላክ ሆይ፣ እርዳታ ለማግኘት የማሰማውን ጩኸት ስማ። ጸሎቴን በትኩረት አዳምጥ።+   ልቤ ተስፋ በቆረጠ* ጊዜከምድር ዳርቻ ወደ አንተ እጮኻለሁ።+ ከእኔ ይልቅ ከፍ ወዳለ ዓለት ምራኝ።+   አንተ መጠጊያዬ ነህና፤ከጠላት የምትጠብቀኝ ጽኑ ግንብ ነህ።+   በድንኳንህ ለዘላለም በእንግድነት እቀመጣለሁ፤+በክንፎችህ ጥላ ሥር እጠለላለሁ።+ (ሴላ)   አምላክ ሆይ፣ ስእለቴን ሰምተሃልና። ስምህን የሚፈሩትን ሰዎች ርስት ሰጥተኸኛል።+   የንጉሡን ሕይወት* ታረዝምለታለህ፤+ዕድሜውም ከትውልድ እስከ ትውልድ ድረስ ይሆናል።   በአምላክ ፊት ለዘላለም ይነግሣል፤*+ታማኝ ፍቅርና ታማኝነት እንዲጠብቁት እዘዝ።*+   እኔም ስእለቴን በየቀኑ ስፈጽም፣+ለስምህ ለዘላለም የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ።+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “በዛለ።”
ቃል በቃል “ቀናት።”
ወይም “ይኖራል።”
ወይም “ላክ።”