መዝሙር 117:1, 2

  • ብሔራት ሁሉ ይሖዋን እንዲያወድሱ የቀረበ ጥሪ

    • የአምላክ ታማኝ ፍቅር ታላቅ ነው (2)

117  ብሔራት ሁሉ፣ ይሖዋን አወድሱት፤+ሕዝቦች* ሁሉ፣ ከፍ ከፍ አድርጉት።+   ለእኛ ያሳየው ታማኝ ፍቅር ታላቅ ነውና፤+የይሖዋ ታማኝነት+ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።+ ያህን አወድሱ!*+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ጎሳዎች።”
ወይም “ሃሌሉያህ!” “ያህ” የይሖዋ ስም አጭር መጠሪያ ነው።