መዝሙር 113:1-9

  • ከፍ ባለ ቦታ ያለው አምላክ ችግረኛውን ያነሳል

    • የይሖዋ ስም ለዘላለም ይወደስ (2)

    • አምላክ ወደ ታች ያጎነብሳል (6)

113  ያህን አወድሱ!* እናንተ የይሖዋ አገልጋዮች፣ ውዳሴ አቅርቡ፤የይሖዋን ስም አወድሱ።   ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም፣የይሖዋ ስም ይወደስ።+   ከፀሐይ መውጫ አንስቶ እስከ መግቢያው ድረስየይሖዋ ስም ይወደስ።+   ይሖዋ ከብሔራት ሁሉ በላይ ከፍ ያለ ነው፤+ክብሩም ከሰማያት በላይ ነው።+   ከፍ ባለ ቦታ እንደሚኖረው*እንደ አምላካችን እንደ ይሖዋ ያለ ማን ነው?+   ሰማይንና ምድርን ለማየት ወደ ታች ያጎነብሳል፤+   ችግረኛውን ከአፈር ያነሳል። ድሃውን ከአመድ ቁልል* ላይ ብድግ ያደርገዋል፤+   ይህም ከታላላቅ ሰዎች፣ይኸውም በሕዝቡ መካከል ካሉ ታላላቅ ሰዎች ጋር ያስቀምጠው ዘንድ ነው።   መሃኒቱ ሴት፣ ደስተኛ የልጆች* እናት+ ሆና እንድትኖርቤት ይሰጣታል። ያህን አወድሱ!*

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ሃሌሉያህ!” “ያህ” የይሖዋ ስም አጭር መጠሪያ ነው።
ወይም “በዙፋን ላይ እንደተቀመጠው።”
“ከቆሻሻ መጣያ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ቃል በቃል “የወንዶች ልጆች።”
ወይም “ሃሌሉያህ!” “ያህ” የይሖዋ ስም አጭር መጠሪያ ነው።