መዝሙር 127:1-5

  • ያለ አምላክ እርዳታ ሁሉ ነገር ከንቱ ድካም ነው

    • “ይሖዋ ቤትን ካልሠራ” (1)

    • ልጆች ከይሖዋ የተገኙ ስጦታዎች ናቸው (3)

ወደ ላይ የመውጣት መዝሙር። የሰለሞን መዝሙር። 127  ይሖዋ ቤትን ካልገነባ፣ግንበኞቹ የሚደክሙት በከንቱ ነው።+ ይሖዋ ከተማን ካልጠበቀ፣+ጠባቂው ንቁ ሆኖ መጠበቁ ከንቱ ድካም ነው።  2  በማለዳ መነሳታችሁ፣እስከ ምሽት ድረስ መሥራታችሁ፣እንዲሁም የዕለት ጉርሳችሁን ለማግኘት መልፋታችሁ ከንቱ ነው፤ምክንያቱም አምላክ የሚወዳቸውን ሰዎች ይንከባከባቸዋል፤ እንቅልፍም ይሰጣቸዋል።+  3  እነሆ፣ ልጆች* ከይሖዋ የተገኙ ውርሻ ናቸው፤+የማህፀንም ፍሬ ከእሱ የሚገኝ ስጦታ ነው።+  4  አንድ ሰው በወጣትነቱ የወለዳቸው ወንዶች ልጆች፣በኃያል ሰው እጅ እንዳሉ ፍላጻዎች ናቸው።+  5  ኮሮጆውን በእነዚህ የሞላ ሰው ደስተኛ ነው።+ እነሱ ፈጽሞ አያፍሩም፤በከተማዋ በር ከጠላቶቻቸው ጋር ይነጋገራሉና።

የግርጌ ማስታወሻዎች

ቃል በቃል “ወንዶች ልጆች።”