መዝሙር 4:1-8

  • በአምላክ በመታመን የቀረበ ጸሎት

    • “ተቆጡ፤ ሆኖም ኃጢአት አትሥሩ” (4)

    • “በሰላም እተኛለሁ” (8)

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ በባለ አውታር መሣሪያዎች የሚታጀብ። የዳዊት ማህሌት። 4  ጻድቅ አምላኬ ሆይ፣+ ስጣራ መልስልኝ። በምጨነቅበት ጊዜ ማምለጫ መንገድ* አዘጋጅልኝ። ቸርነት አሳየኝ፤ ጸሎቴንም ስማ።  2  እናንተ የሰው ልጆች፣ ክብሬን ወደ ውርደት የምትለውጡት እስከ መቼ ነው? ከንቱ ነገሮችን የምትወዱት እስከ መቼ ነው? ሐሰትንስ የምትሹት እስከ መቼ ነው? (ሴላ)  3  ይሖዋ ለእሱ ታማኝ የሆነውን ሰው ልዩ በሆነ መንገድ እንደሚይዘው እወቁ፤*ይሖዋ በጠራሁት ጊዜ ይሰማኛል።  4  ተቆጡ፤ ሆኖም ኃጢአት አትሥሩ።+ የምትናገሩትን በመኝታችሁ ላይ ሳላችሁ በልባችሁ ተናገሩ፤ ጸጥም በሉ። (ሴላ)  5  የጽድቅ መሥዋዕቶች አቅርቡ፤በይሖዋም ታመኑ።+  6  “መልካም ነገር ማን ያሳየናል?” የሚሉ ብዙዎች አሉ። ይሖዋ ሆይ፣ የፊትህን ብርሃን በላያችን አብራ።+  7  የተትረፈረፈ እህል ከሰበሰቡና አዲስ የወይን ጠጅ በብዛት ካመረቱ ሰዎች ይበልጥልቤ በሐሴት እንዲሞላ አደረግክ።  8  በሰላም እተኛለሁ፤ አንቀላፋለሁም፤+ይሖዋ ሆይ፣ ተረጋግቼ እንድኖር የምታደርገኝ አንተ ብቻ ነህና።+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ቃል በቃል “ሰፊ ቦታ።”
ወይም “ለእሱ ታማኝ የሆነውን ሰው ይለያል፤ ለእሱ ታማኝ የሆነውን ሰው ለራሱ ይለያል።”