መዝሙር 34:1-22
ዳዊት በአቢሜሌክ* ፊት አእምሮውን የሳተ መስሎ በመቅረቡ+ አባሮ ባስወጣው ጊዜ የዘመረው መዝሙር።
א [አሌፍ]
34 ይሖዋን ሁልጊዜ አወድሰዋለሁ፤ውዳሴው ምንጊዜም ከአፌ አይለይም።
ב [ቤት]
2 በይሖዋ እኩራራለሁ፤*+የዋሆች ሰምተው ሐሴት ያደርጋሉ።
ג [ጊሜል]
3 ይሖዋን ከእኔ ጋር አወድሱት፤+በኅብረት ስሙን ከፍ ከፍ እናድርግ።
ד [ዳሌት]
4 ይሖዋን ጠየቅኩት፤ እሱም መለሰልኝ።+
ከምፈራው ነገር ሁሉ ታደገኝ።+
ה [ሄ]
5 እሱን ተስፋ ያደረጉ በደስታ ፈኩ፤ፊታቸው ፈጽሞ ለኀፍረት አይዳረግም።
ז [ዛየን]
6 ይህ ችግረኛ ተጣራ፤ ይሖዋም ሰማው።
ከጭንቀቱ ሁሉ ገላገለው።+
ח [ኼት]
7 የይሖዋ መልአክ አምላክን በሚፈሩ ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፤+ደግሞም ይታደጋቸዋል።+
ט [ቴት]
8 ይሖዋ ጥሩ መሆኑን ቅመሱ፤ እዩም፤+እሱን መጠጊያ የሚያደርግ ሰው ደስተኛ ነው።
י [ዮድ]
9 ቅዱሳን አገልጋዮቹ ሁሉ፣ ይሖዋን ፍሩ፤እሱን የሚፈሩ የሚያጡት ነገር የለምና።+
כ [ካፍ]
10 ብርቱ ደቦል አንበሶች እንኳ የሚበሉት አጥተው ይራባሉ፤ይሖዋን የሚሹ ግን መልካም ነገር አይጎድልባቸውም።+
ל [ላሜድ]
11 ልጆቼ ሆይ፣ ኑ፣ አዳምጡኝ፤ይሖዋን መፍራት አስተምራችኋለሁ።+
מ [ሜም]
12 ከእናንተ መካከል በሕይወት የሚደሰት፣ብዙ መልካም ዘመን ማየት የሚወድስ ማን ነው?+
נ [ኑን]
13 እንግዲያው ምላስህን ከክፉ ነገር ጠብቅ፤+በከንፈሮችህም ከማታለል ተቆጠብ።+
ס [ሳሜኽ]
14 ክፉ ከሆነ ነገር ራቅ፤ መልካም የሆነውንም አድርግ፤+ሰላምን ፈልግ፤ ተከተለውም።+
ע [አይን]
15 የይሖዋ ዓይኖች ጻድቃንን ይመለከታሉ፤+ጆሮዎቹም እርዳታ ለማግኘት የሚያሰሙትን ጩኸት ይሰማሉ።+
פ [ፔ]
16 ሆኖም የክፉዎችን መታሰቢያ ሁሉ ከምድር ለማጥፋት፣የይሖዋ ፊት በእነሱ ላይ ነው።+
צ [ጻዴ]
17 ጻድቃን ጮኹ፤ ይሖዋም ሰማቸው፤+ከጭንቀታቸውም ሁሉ ገላገላቸው።+
ק [ኮፍ]
18 ይሖዋ ልባቸው ለተሰበረ ቅርብ ነው፤+መንፈሳቸው የተደቆሰባቸውንም* ያድናል።+
ר [ረሽ]
19 የጻድቅ ሰው መከራ* ብዙ ነው፤+ይሖዋ ግን ከመከራው ሁሉ ይታደገዋል።+
ש [ሺን]
20 አጥንቶቹን ሁሉ ይጠብቃል፤አንዳቸውም ቢሆኑ አልተሰበሩም።+
ת [ታው]
21 ክፉ ሰው በአደጋ ይሞታል፤ጻድቁን የሚጠሉ ሰዎችም ይፈረድባቸዋል።
22 ይሖዋ የአገልጋዮቹን ሕይወት* ይዋጃል፤እሱን መጠጊያ የሚያደርጉ ሁሉ አይፈረድባቸውም።+
የግርጌ ማስታወሻዎች
^ ይህ የንጉሥ አንኩስ የማዕረግ ስም እንደሆነ ይታመናል።
^ ወይም “ነፍሴ በይሖዋ ትኩራራለች።”
^ ወይም “ተስፋ የቆረጡትንም።”
^ ወይም “ጭንቀት።”
^ ወይም “ነፍስ።”