መዝሙር 88:1-18

  • ከሞት ለመዳን የቀረበ ጸሎት

    • ‘ሕይወቴ በመቃብር አፋፍ ላይ ነች’ (3)

    • ‘በየማለዳው ወደ አንተ እጸልያለሁ’ (13)

መዝሙር። የቆሬ ልጆች+ ማህሌት። ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ በማሃላት ቅኝት፤* በመቀባበል የሚዘመር። የዛራዊው የሄማን+ ማስኪል።* 88  የመዳኔ አምላክ የሆንከው ይሖዋ ሆይ፣+በቀን እጮኻለሁ፤በሌሊትም በፊትህ እቀርባለሁ።+   ጸሎቴ ወደ አንተ ይድረስ፤+እርዳታ ለማግኘት የማሰማውን ጩኸት ለማዳመጥ ጆሮህን አዘንብል።*+   ነፍሴ* በመከራ ተሞልታለችና፤+ሕይወቴም በመቃብር* አፋፍ ላይ ነች።+   አሁንም እንኳ ወደ ጉድጓድ* ከሚወርዱ ሰዎች ጋር ተቆጥሬአለሁ፤+ምስኪን ሰው* ሆንኩ፤+   ተገድለው በመቃብር ውስጥ እንደተጋደሙ፣ከእንግዲህ ፈጽሞ እንደማታስታውሳቸውናየአንተ እንክብካቤ* እንደተቋረጠባቸው ሰዎች፣በሙታን መካከል ተተውኩ።   አዘቅት ውስጥ ከተትከኝ፤በጨለማ በተዋጠ ስፍራ፣ ጥልቅ በሆነ ጉድጓድ ውስጥ አኖርከኝ።   በላዬ ላይ ያረፈው ቁጣህ እጅግ ከብዶኛል፤+በኃይለኛ ማዕበልህም አጥለቀለቅከኝ። (ሴላ)   የሚያውቁኝን ሰዎች ከእኔ አራቅክ፤+በእነሱ ፊት አስጸያፊ ነገር አደረግከኝ። ወጥመድ ውስጥ ገብቻለሁ፤ ማምለጥም አልቻልኩም።   ከደረሰብኝ ጉስቁልና የተነሳ ዓይኔ ፈዘዘ።+ ይሖዋ ሆይ፣ ቀኑን ሙሉ አንተን እጣራለሁ፤+እጆቼንም ወደ አንተ እዘረጋለሁ። 10  ለሙታን ድንቅ ሥራዎች ታከናውናለህ? በሞት የተረቱትስ ተነስተው ሊያወድሱህ ይችላሉ?+ (ሴላ) 11  ታማኝ ፍቅርህ በመቃብር፣ታማኝነትህስ በጥፋት ቦታ* ይታወጃል? 12  ያከናወንከው ድንቅ ሥራ በጨለማ፣ጽድቅህስ በተረሱ ሰዎች ምድር ይታወቃል?+ 13  ይሖዋ ሆይ፣ እኔ ግን እርዳታ ለማግኘት አሁንም ወደ አንተ እጮኻለሁ፤+ጸሎቴም በየማለዳው ወደ አንተ ትደርሳለች።+ 14  ይሖዋ ሆይ፣ ፊት የምትነሳኝ ለምንድን ነው?*+ ፊትህንስ ከእኔ የምትሰውረው ለምንድን ነው?+ 15  እኔ ከልጅነቴ ጀምሮየተጎሳቆልኩና ለመጥፋት የተቃረብኩ ነኝ፤+እንዲደርሱብኝ ከፈቀድካቸው አስከፊ ነገሮች የተነሳ ደንዝዣለሁ። 16  የሚነደው ቁጣህ በላዬ ላይ ወረደ፤+አንተ ያመጣህብኝ ሽብር አጠፋኝ። 17  ቀኑን ሙሉ እንደ ውኃ ከበበኝ፤በሁሉም አቅጣጫ* ከቦ መውጫ አሳጣኝ። 18  ወዳጆቼንና ባልንጀሮቼን ከእኔ አራቅክ፤+ጓደኛዬ ጨለማ ብቻ ሆኖ ቀረ።

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ጎንበስ ብለህ ስማኝ።”
ወይም “በሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ወይም “አቅም እንዳጣ ሰው።”
ወይም “መቃብር።”
ቃል በቃል “እጅ።”
ወይም “በአባዶን።”
ወይም “ነፍሴን ፊት የምትነሳት ለምንድን ነው?”
“በአንድ ጊዜ” ማለትም ሊሆን ይችላል።