መዝሙር 133:1-3

  • በአንድነት አብሮ መኖር

    • በአሮን ራስ ላይ እንደፈሰሰ ዘይት (2)

    • እንደ ሄርሞን ጤዛ (3)

ወደ ላይ የመውጣት መዝሙር። የዳዊት መዝሙር። 133  እነሆ፣ ወንድሞች በአንድነት አብረው ቢኖሩምንኛ መልካም ነው! ምንኛስ ደስ ያሰኛል!+   በራስ ላይ ፈስሶ እስከ ጢም እንደሚዘልቅ፣በአሮን ጢም+ ላይ እንደሚወርድ፣እስከ ልብሱ ኮሌታ ድረስ እንደሚፈስጥሩ ዘይት ነው።+   በጽዮን ተራሮች+ ላይ እንደሚወርድ፣እንደ ሄርሞን+ ጤዛ ነው። በዚያ ይሖዋ በረከቱን ይኸውምየዘላለም ሕይወትን አዟል።

የግርጌ ማስታወሻዎች