መዝሙር 48:1-14

  • ጽዮን፣ የታላቁ ንጉሥ ከተማ

    • “የምድር ሁሉ ደስታ” (2)

    • ከተማዋንና ማማዎቿን በሚገባ አጢኑ (11-13)

መዝሙር። የቆሬ ልጆች+ ማህሌት። 48  ይሖዋ ታላቅ ነው፤በአምላካችን ከተማ፣ በቅዱስ ተራራው እጅግ ሊወደስ ይገባዋል።   በከፍታ ቦታ ላይ ተውባ የምትታየው፣ የምድር ሁሉ ደስታ፣+በስተ ሰሜን ርቃ የምትገኘው የጽዮን ተራራ ነች፤ደግሞም የታላቁ ንጉሥ ከተማ ነች።+   አምላክ በማይደፈሩ ማማዎቿ ውስጥአስተማማኝ መጠጊያ መሆኑን አስመሥክሯል።+   እነሆ፣ ነገሥታት ተሰብስበዋልና፤*አንድ ላይ ሆነው ገሰገሱ።   ከተማዋን ባዩአት ጊዜ ተገረሙ። ደንግጠውም ፈረጠጡ።   በዚያም በፍርሃት ተንቀጠቀጡ፤እንደምትወልድ ሴት ጭንቅ ያዛቸው።   የተርሴስን መርከቦች በምሥራቅ ነፋስ ሰባበርክ።   የሰማነውን ነገር፣ በሠራዊት ጌታ በይሖዋ ከተማይኸውም በአምላካችን ከተማ አሁን በገዛ ዓይናችን አይተናል። አምላክ ለዘላለም ያጸናታል።+ (ሴላ)   አምላክ ሆይ፣ በቤተ መቅደስህ ውስጥ ሆነንስለ ታማኝ ፍቅርህ እናሰላስላለን።+ 10  አምላክ ሆይ፣ እንደ ስምህ ሁሉ ውዳሴህምእስከ ምድር ዳርቻ ይደርሳል።+ ቀኝ እጅህ በጽድቅ ተሞልቷል።+ 11  ከፍርድህ የተነሳ የጽዮን ተራራ+ ደስ ይበላት፤የይሁዳ ከተሞችም* ሐሴት ያድርጉ።+ 12  በጽዮን ዙሪያ ሂዱ፤ በዙሪያዋም ተጓዙ፤ማማዎቿን ቁጠሩ።+ 13  የመከላከያ ግንቦቿን*+ ልብ ብላችሁ ተመልከቱ። ለመጪዎቹ ትውልዶች መናገር ትችሉ ዘንድ፣የማይደፈሩ ማማዎቿን በሚገባ አጢኑ። 14  ይህ አምላክ፣ ለዘላለም አምላካችን ነውና።+ እስከ ወዲያኛው* ይመራናል።+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “በቀጠሮ ተገናኝተዋልና።”
ቃል በቃል “ሴቶች ልጆችም።”
ወይም “የማይደፈሩ ግንቦቿን።”
“እስክንሞት ድረስ” ማለትም ሊሆን ይችላል።