መዝሙር 25:1-22

  • መመሪያና ምሕረት ለማግኘት የቀረበ ጸሎት

    • ‘ጎዳናህን አስተምረኝ’ (4)

    • “ከይሖዋ ጋር የጠበቀ ወዳጅነት” መመሥረት (14)

    • ‘ኃጢአቴን ሁሉ ይቅር በል’ (18)

የዳዊት መዝሙር። א [አሌፍ] 25  ይሖዋ ሆይ፣ አንተን እማጸናለሁ።* ב [ቤት]   አምላኬ ሆይ፣ በአንተ እታመናለሁ፤+ለኀፍረት እንድዳረግ አትፍቀድ።+ ጠላቶቼ በደረሰብኝ መከራ አይፈንድቁ።+ ג [ጊሜል]   አንተን ተስፋ የሚያደርግ ሁሉ በፍጹም አያፍርም፤+ያላንዳች ምክንያት ክህደት የሚፈጽሙ ግን ለኀፍረት ይዳረጋሉ።+ ד [ዳሌት]   ይሖዋ ሆይ፣ መንገድህን አሳውቀኝ፤+ጎዳናህንም አስተምረኝ።+ ה []   አንተ አዳኝ አምላኬ ስለሆንክበእውነትህ እንድመላለስ አድርገኝ፤ አስተምረኝም።+ ז [ዋው] ቀኑን ሙሉ አንተን ተስፋ አደርጋለሁ። ז [ዛየን]   ይሖዋ ሆይ፣ ምንጊዜም ታሳያቸው የነበሩትን*+ምሕረትህንና ታማኝ ፍቅርህን አስታውስ።+ ח [ኼት]   በወጣትነቴ የሠራኋቸውን ኃጢአቶችና በደሎች አታስብብኝ። ይሖዋ ሆይ፣ ለጥሩነትህ ስትል+እንደ ታማኝ ፍቅርህ መጠን አስበኝ።+ ט [ቴት]   ይሖዋ ጥሩና ቀና ነው።+ ኃጢአተኞችን ሊኖሩበት የሚገባውን መንገድ የሚያስተምራቸው ለዚህ ነው።+ י [ዮድ]   የዋሆችን በትክክለኛ መንገድ* ይመራቸዋል፤+እንዲሁም ለየዋሆች መንገዱን ያስተምራል።+ כ [ካፍ] 10  የይሖዋ መንገዶች ሁሉ፣ ቃል ኪዳኑንና+ ማሳሰቢያዎቹን+ ለሚጠብቁ፣ታማኝ ፍቅር የሚንጸባረቅባቸውና እምነት የሚጣልባቸው ናቸው። ל [ላሜድ] 11  ይሖዋ ሆይ፣ ኃጢአቴ ታላቅ ቢሆንም እንኳለስምህ ስትል ይቅር በለኝ።+ מ [ሜም] 12  ይሖዋን የሚፈራ ሰው ማን ነው?+ መምረጥ ስላለበት መንገድ ያስተምረዋል።+ נ [ኑን] 13  እሱ ጥሩ የሆነውን ነገር ያገኛል፤*+ዘሮቹም ምድርን ይወርሳሉ።+ ס [ሳሜኽ] 14  ከይሖዋ ጋር የጠበቀ ወዳጅነት የሚኖራቸው እሱን የሚፈሩ ሰዎች ናቸው፤+ቃል ኪዳኑንም ያሳውቃቸዋል።+ ע [አይን] 15  ዓይኖቼ ሁልጊዜ ወደ ይሖዋ ያያሉ፤+እግሮቼን ከወጥመድ ያወጣቸዋልና።+ פ [] 16  ብቸኛና ምስኪን ስለሆንኩፊትህን ወደ እኔ መልስ፤ ቸርነትም አሳየኝ። צ [ጻዴ] 17  የልቤ ጭንቀት በዝቷል፤+ከሥቃዬ ገላግለኝ። ר [ረሽ] 18  ጉስቁልናዬንና መከራዬን ተመልከት፤+ኃጢአቴንም ሁሉ ይቅር በል።+ 19  ጠላቶቼ ምን ያህል ብዙ እንደሆኑ ተመልከት፤ምን ያህል አምርረው እንደሚጠሉኝም እይ። ש [ሺን] 20  ሕይወቴን* ጠብቅ፤ አድነኝም።+ አንተን መጠጊያ ስላደረግኩ ለኀፍረት እንድዳረግ አትፍቀድ። ת [ታው] 21  ንጹሕ አቋሜና* ቅንነቴ ይጠብቁኝ፤+አንተን ተስፋ አድርጌአለሁና።+ 22  አምላክ ሆይ፣ እስራኤልን ከጭንቀቱ ሁሉ ታደገው።*

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ነፍሴን ወደ አንተ አነሳለሁ።”
ወይም “ከጥንት ዘመን ጀምሮ የነበሩትን።”
ቃል በቃል “በፍርድ።”
ወይም “ነፍሱ ጥሩ የሆነውን ነገር ታገኛለች።”
ወይም “ነፍሴን።”
መዝ 7:8 ላይ የሚገኘውን የግርጌ ማስታወሻ ተመልከት።
ቃል በቃል “ዋጀው።”