መዝሙር 57:1-11

  • ሞገስ ለማግኘት የቀረበ ልመና

    • በአምላክ ክንፎች ሥር መጠለል (1)

    • ጠላቶች በራሳቸው ወጥመድ ውስጥ ገቡ (6)

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ “ጥፋት አታምጣ” በተባለው ቅኝት። የዳዊት መዝሙር። ሚክታም።* ከሳኦል ሸሽቶ ወደ ዋሻ በገባበት ጊዜ።+ 57  ሞገስ አሳየኝ፤ አምላክ ሆይ፣ ሞገስ አሳየኝ፤አንተን መጠጊያ አድርጌአለሁና፤*+መከራው እስኪያልፍ ድረስ በክንፎችህ ጥላ ሥር እጠለላለሁ።+   ወደ ልዑሉ አምላክ፣ለእኔ ሲል መከራውን ወደሚያስቆመው ወደ እውነተኛው አምላክ እጣራለሁ።   ከሰማይ እርዳታ ልኮ ያድነኛል።+ ሊነክሰኝ የሚሞክረውን ሰው እንዳይሳካለት ያደርጋል። (ሴላ) አምላክ ታማኝ ፍቅሩንና ታማኝነቱን ያሳያል።+   አንበሶች ከበውኛል፤*+ሊውጡኝ በሚፈልጉ ሰዎች መካከል ለመተኛት ተገድጃለሁ፤ጥርሳቸው ጦርና ፍላጻ ነው፤ምላሳቸውም የተሳለ ሰይፍ ነው።+   አምላክ ሆይ፣ ከሰማያት በላይ ከፍ ከፍ በል፤ክብርህ በምድር ሁሉ ላይ ይሁን።+   እግሮቼን ለመያዝ ወጥመድ አዘጋጅተዋል፤+ከጭንቅ የተነሳ ጎብጫለሁ።*+ በፊቴ ጉድጓድ ቆፈሩ፤ነገር ግን ራሳቸው ገቡበት።+ (ሴላ)   ልቤ ጽኑ ነው፤አምላክ ሆይ፣ ልቤ ጽኑ ነው።+ እዘምራለሁ፤ ደግሞም አዜማለሁ።   ልቤ* ሆይ፣ ተነሳ። ባለ አውታር መሣሪያ ሆይ፣ አንተም በገና ሆይ፣ ተነሱ። እኔም በማለዳ እነሳለሁ።+   ይሖዋ ሆይ፣ በሕዝቦች መካከል አወድስሃለሁ፤+በብሔራት መካከል የውዳሴ መዝሙር እዘምርልሃለሁ።+ 10  ታማኝ ፍቅርህ ታላቅ ነውና፤ እንደ ሰማያት ከፍ ያለ ነው፤+ታማኝነትህም እስከ ደመናት ድረስ ነው። 11  አምላክ ሆይ፣ ከሰማያት በላይ ከፍ ከፍ በል፤ክብርህ በምድር ሁሉ ላይ ይሁን።+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ነፍሴ አንተን መጠጊያ አድርጋለችና።”
ወይም “ነፍሴ በአንበሶች ተከባለች።”
ወይም “ነፍሴ ከጭንቅ የተነሳ ጎብጣለች።”
ቃል በቃል “ክብሬ።”