መዝሙር 13:1-6

  • የይሖዋን ማዳን መጠባበቅ

    • ‘ይሖዋ ሆይ፣ እስከ መቼ ነው?’ (1, 2)

    • ይሖዋ በእጅጉ ይክሳል (6)

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የዳዊት ማህሌት። 13  ይሖዋ ሆይ፣ የምትረሳኝ እስከ መቼ ነው? ለዘላለም? ፊትህን ከእኔ የምትሰውረው እስከ መቼ ነው?+   ልቤ በየዕለቱ በሐዘን እየተደቆሰ፣በጭንቀት ተውጬ የምኖረው* እስከ መቼ ነው? ጠላቴ በእኔ ላይ የሚያይለው እስከ መቼ ነው?+   ይሖዋ አምላኬ ሆይ፣ ወደ እኔ ተመልከት፤ መልስም ስጠኝ። በሞት እንዳላንቀላፋ ዓይኖቼን አብራልኝ፤   እንዲህ ከሆነ ጠላቴ “አሸነፍኩት!” አይልም፤ ባላጋራዎቼ በእኔ ውድቀት ሐሴት እንዲያደርጉ አትፍቀድ።+   እኔ በበኩሌ በታማኝ ፍቅርህ እታመናለሁ፤+ልቤ በማዳን ሥራህ ሐሴት ያደርጋል።+   በእጅጉ ስለካሰኝ+ ለይሖዋ እዘምራለሁ።

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ነፍሴ በጭንቀት ተውጣ የምትኖረው።”