መዝሙር 90:1-17

  • የአምላክ ዘላለማዊነትና የሰው አጭር ዕድሜ

    • ሺህ ዓመት እንደ ትናንት ቀን ነው (4)

    • የሰው ዕድሜ ከ70-80 ዓመት ነው (10)

    • “ዕድሜያችንን እንዴት መቁጠር እንዳለብን አስተምረን” (12)

የእውነተኛው አምላክ ሰው የሙሴ ጸሎት።+ 90  ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ከትውልድ እስከ ትውልድ መኖሪያችን* ሆነሃል።+  2  ተራሮች ሳይወለዱ፣ምድርንና ዓለምን ከመፍጠርህ*+ በፊት፣ከዘላለም እስከ ዘላለም አንተ አምላክ ነህ።+  3  ሟች የሆነ ሰው ወደ አፈር እንዲመለስ ታደርጋለህ፤“የሰው ልጆች ሆይ፣ ወደ አፈር ተመለሱ”+ ትላለህ።  4  በአንተ ዘንድ ሺህ ዓመት፣ እንዳለፈችው እንደ ትናንት ቀን፣+እንደ አንድ ክፍለ ሌሊትም* ነው።  5  ጠራርገህ ታስወግዳቸዋለህ፤+ እንደ ሕልም ይጠፋሉ፤በማለዳ ሲታዩ እንደሚለመልም ሣር ናቸው።+  6  ጠዋት ላይ ሣሩ ያቆጠቁጣል፤ ደግሞም ይለመልማል፤ምሽት ላይ ግን ጠውልጎ ይደርቃል።+  7  በቁጣህ አልቀናልና፤+ከታላቅ ቁጣህም የተነሳ ተሸብረናል።  8  በደላችንን በፊትህ ታኖራለህ፤*+የደበቅናቸው ነገሮች በፊትህ ብርሃን ተጋልጠዋል።+  9  ከኃይለኛ ቁጣህ የተነሳ ዘመናችን* ይመናመናል፤ዕድሜያችንም ሽው ብሎ ያልፋል።* 10  የዕድሜያችን ርዝማኔ 70 ዓመት ነው፤ለየት ያለ ጥንካሬ ካለን* ደግሞ 80+ ዓመት ቢሆን ነው። ይህም በችግርና በሐዘን የተሞላ ነው፤ፈጥኖ ይነጉዳል፤ እኛም እናልፋለን።+ 11  የቁጣህን ኃይል መረዳት የሚችል ማን ነው? ቁጣህ፣ አንተ መፈራት የሚገባህን ያህል ታላቅ ነው።+ 12  ጥበበኛ ልብ ማግኘት እንችል ዘንድ፣ዕድሜያችንን እንዴት መቁጠር እንዳለብን አስተምረን።+ 13  ይሖዋ ሆይ፣ ተመለስ!+ ይህ ሁኔታ የሚቀጥለው እስከ መቼ ነው?+ ለአገልጋዮችህ ራራላቸው።+ 14  በሕይወት ዘመናችን ሁሉ እልል እንድንልና ሐሴት እንድናደርግ፣+በማለዳ ታማኝ ፍቅርህን አጥግበን።+ 15  ባጎሳቆልከን ዘመን ልክ፣መከራም ባየንባቸው ዓመታት መጠን+ ሐሴት እንዲሰማን አድርገን።+ 16  አገልጋዮችህ ሥራህን ይዩ፤ልጆቻቸውም ግርማህን ይመልከቱ።+ 17  የአምላካችን የይሖዋ ሞገስ በእኛ ላይ ይሁን፤የእጆቻችንን ሥራ ፍሬያማ አድርግልን።* አዎ፣ የእጆቻችንን ሥራ ፍሬያማ አድርግልን።+

የግርጌ ማስታወሻዎች

^ “መጠጊያችን” ማለትም ሊሆን ይችላል።
^ ወይም “አምጠህ ከመውለድህ።”
^ ክፍለ ሌሊት ፀሐይ ከጠለቀችበት አንስቶ እስከምትወጣበት ድረስ ካለው ጊዜ ውስጥ አንድ ሦስተኛውን ይሸፍናል። በመሆኑም እንደ ወቅቱ ሁኔታ፣ አንድ ክፍለ ሌሊት የአራት ሰዓት ገደማ ርዝማኔ ሊኖረው ይችላል።
^ ወይም “በደላችንን ታውቃለህ።”
^ ወይም “ሕይወታችን።”
^ ወይም “እንደ እስትንፋስ ወዲያው ያከትማል።”
^ ወይም “ልዩ ብርታት ቢኖረን።”
^ ወይም “አጽናልን።”