መዝሙር 49:1-20

  • በሀብት መታመን ሞኝነት ነው

    • ሌላውን መዋጀት የሚችል ሰው የለም (7, 8)

    • አምላክ ከመቃብር ይዋጃል (15)

    • ሀብት ከሞት ሊያድን አይችልም (16, 17)

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የቆሬ ልጆች+ ማህሌት። 49  እናንተ ሕዝቦች ሁሉ፣ ይህን ስሙ። በዓለም ላይ* የምትኖሩ ሁሉ፣ ልብ በሉ፤   ታናናሾችም ሆናችሁ ታላላቆች፣*ባለጸጎችና ድሆች፣ ሁላችሁም ስሙ።   አፌ ጥበብን ይናገራል፤በልቤም የማሰላስለው ነገር+ ማስተዋልን ይገልጣል።   ጆሮዬን ወደ ምሳሌ አዘነብላለሁ፤እንቆቅልሼንም በበገና እፈታለሁ።   በአስቸጋሪ ወቅት፣እኔን ለመጣል የሚፈልጉ ሰዎች ክፋት* በከበበኝ ጊዜ ለምን እፈራለሁ?+   በሀብታቸው የሚመኩትን፣+በታላቅ ብልጽግናቸው የሚኩራሩትንም+ ለምን እፈራለሁ?   አንዳቸውም ቢሆኑ ሌላውን ሰው መዋጀት፣ወይም ለእሱ ቤዛ የሚሆን ነገር ለአምላክ መክፈል ጨርሶ አይችሉም፤+   (ለሕይወታቸው* የሚከፈለው የቤዛ* ዋጋ እጅግ ውድ ስለሆነመቼም ቢሆን ከአቅማቸው በላይ ነው)፤   ለዘላለም እንዲኖርና ወደ ጉድጓድ* እንዳይወርድ ቤዛ ሊከፍሉ አይችሉም።+ 10  ጥበበኞች እንኳ ሲሞቱ ያያል፤ሞኞችና ማመዛዘን የሚጎድላቸው ሰዎች አብረው ይጠፋሉ፤+ሀብታቸውንም ለሌሎች ትተውት ያልፋሉ።+ 11  ምኞታቸው ቤቶቻቸው ለዘላለም እንዲኖሩ፣ድንኳናቸውም ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ ነው። ርስታቸውን በራሳቸው ስም ሰይመዋል። 12  ይሁንና የሰው ልጅ የተከበረ ቢሆንም እንኳ በሕይወት አይዘልቅም፤+ከሚጠፉ እንስሳት ምንም አይሻልም።+ 13  የሞኞች መንገድ ይህ ነው፤+እነሱ በሚናገሩት ከንቱ ቃል ተደስተው የሚከተሏቸው ሰዎች መንገድም ይኸው ነው። (ሴላ) 14  ለእርድ እንደሚነዱ በጎች ወደ መቃብር* እንዲወርዱ ተፈርዶባቸዋል። ሞት እረኛቸው ይሆናል፤በማለዳ ቅኖች ይገዟቸዋል።+ ደብዛቸው ይጠፋል፤+በቤተ መንግሥት ፋንታ መቃብር* መኖሪያቸው ይሆናል።+ 15  ሆኖም አምላክ ከመቃብር* እጅ ይዋጀኛል፤*+እሱ ይይዘኛልና። (ሴላ) 16  ሰው ሀብታም ሲሆንናየቤቱ ክብር ሲጨምር አትፍራው፤ 17  በሚሞትበት ጊዜ ከእሱ ጋር አንዳች ነገር ሊወስድ አይችልምና፤+ክብሩም አብሮት አይወርድም።+ 18  በሕይወት ዘመኑ ራሱን* ሲያወድስ ይኖራልና።+ (ስትበለጽግ ሰዎች ያወድሱሃል።)+ 19  መጨረሻ ላይ ግን ከአባቶቹ ትውልድ ጋር ይቀላቀላል። ከዚያ በኋላ ፈጽሞ ብርሃን አያዩም። 20  የተከበረ ቢሆንም እንኳ ይህን የማይረዳ ሰውከሚጠፉ እንስሳት ምንም አይሻልም።+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “በዚህ ሥርዓት።”
ቃል በቃል “የሰው ዘር ወንዶች ልጆችም ሆናችሁ የሰው ወንዶች ልጆች።”
ቃል በቃል “ስህተት።”
ወይም “ለነፍሳቸው።”
ወይም “ሕይወታቸውን ለመቤዠት የሚከፈለው።”
ወይም “መቃብር።”
ወይም “ሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ወይም “ሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ወይም “ሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ወይም “ነፍሴን ይዋጃታል።”
ወይም “ነፍሱን።”