መዝሙር 59:1-17

  • አምላክ ጋሻና መጠጊያ ነው

    • ‘ለከሃዲዎች ምሕረት አታድርግ’ (5)

    • “ስለ ብርታትህ እዘምራለሁ” (16)

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ “ጥፋት አታምጣ” በተባለው ቅኝት። የዳዊት መዝሙር። ሚክታም።* ሳኦል የዳዊትን ቤት* ከበው እንዲጠብቁና እንዲገድሉት ሰዎችን በላከ ጊዜ።+ 59  አምላኬ ሆይ፣ ከጠላቶቼ ታደገኝ፤+በእኔ ላይ ከተነሱት ሰዎች ጠብቀኝ።+  2  ከክፉ አድራጊዎች ታደገኝ፤ከጨካኝ* ሰዎችም አድነኝ።  3  እነሆ፣ እኔን* ለማጥቃት አድፍጠው ይጠብቃሉ፤+ይሖዋ ሆይ፣ ምንም ዓይነት ዓመፅም ሆነ ኃጢአት ሳይገኝብኝብርቱ የሆኑ ሰዎች ያጠቁኛል።+  4  የሠራሁት ጥፋት ባይኖርም እኔን ለማጥቃት ተጣደፉ፤ ደግሞም ተዘጋጁ። ወደ አንተ ስጣራ ተነስ፤ ተመልከተኝም።  5  የሠራዊት አምላክ ይሖዋ ሆይ፣ አንተ የእስራኤል አምላክ ነህና።+ ብሔራትን ሁሉ ለመመርመር ተነስ። ተንኮለኛ ለሆኑ ከሃዲዎች ሁሉ ምሕረት አታድርግ።+ (ሴላ)  6  በየምሽቱ ተመልሰው ይመጣሉ፤+እንደ ውሾች እያጉረመረሙ* በከተማዋ ዙሪያ ያደባሉ።+  7  ከአፋቸው የሚዥጎደጎደውን* ተመልከት፤ከንፈሮቻቸው እንደ ሰይፍ ናቸው፤+“ማን ይሰማል?” ይላሉና።+  8  ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ግን ትስቅባቸዋለህ፤+ብሔራትን ሁሉ ታላግጥባቸዋለህ።+  9  ብርታቴ ሆይ፣ አንተን እጠባበቃለሁ፤+አምላክ አስተማማኝ መጠጊያዬ ነውና።+ 10  ታማኝ ፍቅር የሚያሳየኝ አምላክ ይረዳኛል፤+አምላክ ጠላቶቼን በድል አድራጊነት ስሜት እንዳያቸው ያደርገኛል።+ 11  ሕዝቤ ይህን እንዳይረሳ አትግደላቸው። በኃይልህ እንዲቅበዘበዙ አድርጋቸው፤ጋሻችን ይሖዋ ሆይ፣ ለውድቀት ዳርጋቸው።+ 12  ከአፋቸው ኃጢአትና ከከንፈራቸው ቃል፣ከሚናገሩት እርግማንና የማታለያ ቃል የተነሳበኩራታቸው ይጠመዱ።+ 13  በቁጣህ አጥፋቸው፤+ከሕልውና ውጭ እንዲሆኑ ደምስሳቸው፤አምላክ ያዕቆብንና መላውን ምድር በመግዛት ላይ እንደሆነ አሳውቃቸው።+ (ሴላ) 14  ምሽት ላይ ተመልሰው ይምጡ፤እንደ ውሾች እያጉረመረሙ* በከተማዋ ዙሪያ ያድቡ።+ 15  ምግብ ፍለጋ ወዲያ ወዲህ ይንከራተቱ፤+በልተውም አይጥገቡ፤ የሚያርፉበት ቦታም ይጡ። 16  እኔ ግን ስለ ብርታትህ እዘምራለሁ፤+በማለዳ ስለ ታማኝ ፍቅርህ በደስታ እናገራለሁ። አንተ አስተማማኝ መጠጊያዬ፣ደግሞም በጭንቀቴ ቀን መሸሸጊያዬ ነህና።+ 17  ብርታቴ ሆይ፣ ለአንተ የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ፤+ታማኝ ፍቅር የሚያሳየኝ አምላክ አስተማማኝ መጠጊያዬ ነውና።+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ቃል በቃል “ቤቱን።”
ወይም “ደም ከተጠሙ።”
ወይም “ነፍሴን።”
ወይም “እየጮኹ።”
ወይም “የሚፈልቀውን።”
ወይም “እየጮኹ።”