መዝሙር 52:1-9

  • በአምላክ ታማኝ ፍቅር መታመን

    • በክፋት የሚኩራሩ ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው (1-5)

    • ፈሪሃ አምላክ የሌላቸው ሰዎች በሀብት ይታመናሉ (7)

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። ማስኪል።* የዳዊት መዝሙር፤ ኤዶማዊው ዶይቅ ወደ ሳኦል ሄዶ፣ ዳዊት ወደ አሂሜሌክ ቤት መጥቶ እንደነበር በነገረው ጊዜ።+ 52  አንተ ኃያል፣ መጥፎ በሆነው ተግባርህ የምትኩራራው ለምንድን ነው?+ የአምላክ ታማኝ ፍቅር ዘላቂ እንደሆነ አታውቅም?+  2  ምላስህ እንደ ምላጭ የተሳለ ነው፤+ጥፋትን ይሸርባል፤ ተንኮልንም ያቀነባብራል።+  3  መልካም ከሆነው ነገር ይልቅ ክፋትን፣ትክክል የሆነውን ነገር ከመናገር ይልቅ ሐሰትን ትወዳለህ። (ሴላ)  4  አንተ አታላይ ምላስ!ጎጂ ቃልን ሁሉ ትወዳለህ።  5  በመሆኑም አምላክ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ያንኮታኩትሃል፤+መንጭቆ ይወስድሃል፤ ከድንኳንህም ጎትቶ ያወጣሃል፤+ከሕያዋን ምድር ይነቅልሃል።+ (ሴላ)  6  ጻድቃንም ይህን አይተው በፍርሃት* ይዋጣሉ፤+በእሱም ላይ ይስቃሉ።+  7  “እንዲህ ያለ ሰው አምላክን መጠጊያው* አያደርግም፤+ይልቁንም በታላቅ ሀብቱ ይታመናል፤+ራሱ በሚጠነስሰውም ሴራ* ይመካል።”*  8  እኔ ግን በአምላክ ቤት እንዳለ የለመለመ የወይራ ዛፍ እሆናለሁ፤ለዘላለም በአምላክ ታማኝ ፍቅር እታመናለሁ።+  9  እርምጃ ስለወሰድክ ለዘላለም አወድስሃለሁ፤+መልካም ነውና፣ በታማኝ አገልጋዮችህ ፊትበስምህ ተስፋ አደርጋለሁ።+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “በአክብሮታዊ ፍርሃት።”
ወይም “ምሽጉ።”
ቃል በቃል “ራሱ በሚያመጣው መከራ።”
ወይም “ይጠለላል።”