መዝሙር 5:1-12

  • ይሖዋ ለጻድቅ መጠጊያ ነው

    • አምላክ ክፋትን ይጠላል (4, 5)

    • “በጽድቅህ ምራኝ” (8)

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ በኔሂሎት።* የዳዊት ማህሌት። 5  ይሖዋ ሆይ፣ ቃሌን አዳምጥ፤+መቃተቴን ልብ በል።  2  ንጉሤና አምላኬ ሆይ፣ ወደ አንተ እጸልያለሁና፣ለእርዳታ የማሰማውን ጩኸት በትኩረት አዳምጥ።  3  ይሖዋ ሆይ፣ በማለዳ ድምፄን ትሰማለህ፤+ያሳሰበኝን ነገር በማለዳ ለአንተ እናገራለሁ፤+ በተስፋም እጠባበቃለሁ።  4  አንተ በክፋት የምትደሰት አምላክ አይደለህምና፤+ክፉ ሰው ከአንተ ጋር አይቀመጥም።+  5  እብሪተኛ ሰው በፊትህ አይቆምም። መጥፎ ምግባር ያላቸውን ሁሉ ትጠላለህ፤+  6  ውሸት የሚናገሩትን ታጠፋለህ።+ ይሖዋ ዓመፀኞችንና አታላዮችን* ይጸየፋል።+  7  እኔ ግን ታላቅ ከሆነው ታማኝ ፍቅርህ የተነሳ+ ወደ ቤትህ እገባለሁ፤+አንተን በመፍራት* ቅዱስ ወደሆነው ቤተ መቅደስህ እሰግዳለሁ።+  8  ይሖዋ ሆይ፣ ጠላቶቼ በዙሪያዬ ስላሉ በጽድቅህ ምራኝ፤ከመንገድህ ላይ እንቅፋቶችን አስወግድልኝ።+  9  የሚሉት ነገር ሁሉ ሊታመን አይችልም፤ውስጣቸው በተንኮል የተሞላ ነው።ጉሮሯቸው የተከፈተ መቃብር ነው፤በምላሳቸው ይሸነግላሉ።*+ 10  አምላክ ግን ይፈርድባቸዋል፤የገዛ ራሳቸው ዕቅድ ለጥፋት ይዳርጋቸዋል።+ ከበደላቸው ብዛት የተነሳ ይባረሩ፤በአንተ ላይ ዓምፀዋልና። 11  አንተን መጠጊያ የሚያደርጉ ሁሉ ግን ሐሴት ያደርጋሉ፤+ምንጊዜም በደስታ እልል ይላሉ። ሊጎዷቸው ከሚፈልጉ ሰዎች ትጠብቃቸዋለህ፤ስምህን የሚወዱም በአንተ ሐሴት ያደርጋሉ። 12  ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ጻድቅ የሆነውን ሁሉ ትባርካለህና፤ሞገስህ እንደ ትልቅ ጋሻ ይሆንላቸዋል።+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ደም አፍሳሽና አታላይ የሆነን ሰው።”
ወይም “ለአንተ አክብሮታዊ ፍርሃት በማሳየት።”
ወይም “በለሰለሰ አንደበት ይናገራሉ።”