መዝሙር 122:1-9

  • ለኢየሩሳሌም ሰላም የቀረበ ጸሎት

    • ወደ ይሖዋ ቤት መሄድ የሚያስገኘው ደስታ (1)

    • አንድ ወጥ ሆና የተገነባች ከተማ (3)

ወደ ላይ የመውጣት መዝሙር። የዳዊት መዝሙር። 122  “ወደ ይሖዋ ቤት እንሂድ” ባሉኝ ጊዜ እጅግ ደስ አለኝ።+  2  ኢየሩሳሌም ሆይ፣ አሁን በበሮችሽ ገብተንከውስጥ ቆመናል።+  3  ኢየሩሳሌም አንድ ወጥ ሆናእንደተገነባች ከተማ ናት።+  4  ለእስራኤል በተሰጠው ማሳሰቢያ መሠረት፣ነገዶቹ ይኸውም የያህ* ነገዶች፣ለይሖዋ ስም ምስጋና ለማቅረብወደዚያ ወጥተዋል።+  5  በዚያ የፍርድ ዙፋኖች፣የዳዊት ቤት ዙፋኖች+ ተቀምጠዋልና።+  6  ለኢየሩሳሌም ሰላም ጸልዩ።+ አንቺ ከተማ ሆይ፣ አንቺን የሚወዱ ከስጋት ነፃ ይሆናሉ።  7  በመከላከያ ግንቦችሽ* ውስጥ ሰላም ለዘለቄታው ይኑር፤በማይደፈሩ ማማዎችሽ ውስጥ የተረጋጋ ሁኔታ ይስፈን።  8  እንግዲህ ለወንድሞቼና ለወዳጆቼ ስል “በውስጥሽ ሰላም ይስፈን” እላለሁ።  9  ለአምላካችን ለይሖዋ ቤት ስል+ለአንቺ መልካም ነገር እሻለሁ።

የግርጌ ማስታወሻዎች

“ያህ” የይሖዋ ስም አጭር መጠሪያ ነው።
ወይም “በተመሸጉ ቅጥሮችሽ።”