መዝሙር 140:1-13

  • ኃያል አዳኝ የሆነው ይሖዋ

    • ክፉዎች እንደ እባብ ናቸው (3)

    • ጨካኞች ጥፋት ይደርስባቸዋል (11)

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የዳዊት ማህሌት። 140  ይሖዋ ሆይ፣ ከክፉ ሰዎች ታደገኝ፤ከጨካኞችም ጠብቀኝ፤+  2  እነሱ በልባቸው ክፉ ነገር ይጠነስሳሉ፤+ደግሞም ቀኑን ሙሉ ጠብ ይጭራሉ።  3  እንደ እባብ ምላሳቸውን ያሾላሉ፤+ከከንፈራቸው ኋላ የእፉኝት መርዝ አለ።+ (ሴላ)  4  ይሖዋ ሆይ፣ ከክፉዎች እጅ አድነኝ፤+እኔን ጠልፈው ለመጣል ከሚያሴሩጨካኝ ሰዎች ጠብቀኝ።  5  ትዕቢተኞች በስውር ወጥመድ አስቀመጡብኝ፤ከመንገዱ አጠገብ የመረባቸውን ገመድ ዘረጉብኝ።+ አሽክላም አስቀመጡብኝ።+ (ሴላ)  6  ይሖዋን እንዲህ እለዋለሁ፦ “አንተ አምላኬ ነህ። ይሖዋ ሆይ፣ እርዳታ ለማግኘት የማቀርበውን ልመና ስማ።”+  7  ኃያል አዳኜ የሆንከው ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣በጦርነት ቀን ራሴን ትከልላለህ።+  8  ይሖዋ ሆይ፣ የክፉዎች ምኞት እንዲሳካ አታድርግ። ራሳቸውን ከፍ ከፍ እንዳያደርጉ፣ ሴራቸው እንዲሰምር አትፍቀድ።+ (ሴላ)  9  ዙሪያዬን የከበቡኝን ሰዎች ራስ፣የገዛ ከንፈራቸው የተናገረው ክፋት ይሸፍነው።+ 10  የእሳት ፍም በላያቸው ይውረድ።+ መነሳት እንዳይችሉ ወደ እሳት፣ወደ ጥልቅ ጉድጓዶች* ይወርወሩ።+ 11  ስም አጥፊ በምድር* ላይ አንዳች ቦታ አያግኝ።+ ጨካኞችን ክፋት አሳዶ ይምታቸው። 12  ይሖዋ ለችግረኛው እንደሚሟገትናለድሃው ፍትሕ እንደሚያሰፍን አውቃለሁ።+ 13  በእርግጥ ጻድቃን ለስምህ ምስጋና ያቀርባሉ፤ቅኖችም በፊትህ ይኖራሉ።+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ውኃ ወዳለባቸው ጉድጓዶች።”
ወይም “በአገሪቱ።”