መዝሙር 93:1-5

  • ግርማ የተላበሰው የይሖዋ አገዛዝ

    • “ይሖዋ ነገሠ!” (1)

    • ‘ማሳሰቢያዎችህ አስተማማኝ ናቸው’ (5)

93  ይሖዋ ነገሠ!+ ግርማ ተጎናጽፏል፤ይሖዋ ብርታት ለብሷል፤እንደ ቀበቶ ታጥቆታል። ምድር* በጽኑ ተመሥርታለች፤ልትናወጥ አትችልም።   ዙፋንህ ከብዙ ዘመናት በፊት ጸንቶ የተመሠረተ ነው፤+አንተ ከዘላለም እስከ ዘላለም አለህ።+   ይሖዋ ሆይ፣ ወንዞቹ ጎረፉ፤ወንዞቹ ጎረፉ፤ አስገመገሙም፤ወንዞቹ ይጎርፋሉ፤ ደግሞም በኃይል ይላተማሉ።   ከብዙ ውኃዎች ድምፅ፣ኃይለኛ ከሆነው የባሕር ማዕበልም በላይ፣+ይሖዋ ከፍ ባለ ቦታ ግርማ ተጎናጽፏል።+   ማሳሰቢያዎችህ እጅግ አስተማማኝ ናቸው።+ ይሖዋ ሆይ፣ ቤትህ ለዘላለሙ በቅድስና ያጌጠ ነው።*+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ፍሬያማ የሆነችው ምድር።”
ወይም “ቅድስና ይገባዋል።”