መዝሙር 12:1-8

  • ይሖዋ እርምጃ ለመውሰድ ይነሳል

    • የአምላክ ቃል የጠራ ነው (6)

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ በሸሚኒት ቅኝት።* የዳዊት ማህሌት። 12  ይሖዋ ሆይ፣ አንድም ታማኝ ሰው ስለሌለ አድነኝ፤ከሰው ልጆች መካከል ታማኞች ጠፍተዋል።  2  እርስ በርሳቸው ውሸት ይነጋገራሉ፤በከንፈራቸው ይሸነግላሉ፤* አታላይ በሆነ ልብም* ይናገራሉ።+  3  ይሖዋ የሚሸነግልን ከንፈር ሁሉ፣ጉራ የሚነዛውንም ምላስ ይቆርጣል፤+  4  እነሱ “በምላሳችን እንረታለን። አንደበታችንን እንዳሻን እንጠቀምበታለን፤በእኛ ላይ ጌታ ሊሆን የሚችል ማን ነው?” ይላሉ።+  5  “የተጎሳቆሉት ሰዎች በመጨቆናቸው፣ድሆችም በመቃተታቸው፣+እርምጃ ለመውሰድ እነሳለሁ” ይላል ይሖዋ። “በንቀት ዓይን ከሚመለከቷቸው* ሁሉ እታደጋቸዋለሁ።”  6  የይሖዋ ቃል የጠራ ነው፤+ከሸክላ በተሠራ ምድጃ* እንደተጣራ ብር ሰባት ጊዜ የነጠረ ነው።  7  ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ትጋርዳቸዋለህ፤+እያንዳንዳቸውን ከዚህ ትውልድ ለዘላለም ትጠብቃቸዋለህ።  8  የሰው ልጆች ብልሹ ምግባርን ስለሚያስፋፉ፣ክፉዎች እንዳሻቸው ይፈነጫሉ።+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ቃል በቃል “በለስላሳ ከንፈር ይናገራሉ።”
ቃል በቃል “በልብና በልብም።”
ወይም “ጉራ ከሚነዙባቸው።”
“መሬት ላይ በተተከለ የማቅለጫ ምድጃ” ማለትም ሊሆን ይችላል።