መዝሙር 142:1-7

  • ከአሳዳጆቹ እንዲታደገው ያቀረበው ጸሎት

    • “ሸሽቼ ማምለጥ የምችልበት ቦታ የለም” (4)

    • “ያለኸኝ አንተ ብቻ ነህ” (5)

ማስኪል።* ዳዊት ዋሻ ውስጥ በነበረበት ጊዜ+ የዘመረው መዝሙር። ጸሎት። 142  ድምፄን አውጥቼ እርዳታ ለማግኘት ወደ ይሖዋ እጣራለሁ፤+ሞገስ እንዲያሳየኝ ይሖዋን እማጸናለሁ።  2  የሚያሳስበኝን ነገር በፊቱ አፈስሳለሁ፤የውስጤን ጭንቀት በፊቱ እናገራለሁ፤+  3  መንፈሴ* በውስጤ ሲዝል፣ እሱን እማጸናለሁ። በዚህ ጊዜ ጎዳናዬን ትመለከታለህ።+ በምሄድበት መንገድ ላይበስውር ወጥመድ ዘረጉብኝ።  4  ቀኝ እጄን ተመልከት፤ስለ እኔ ግድ የሚሰጠው* ሰው እንደሌለ እይ።+ ሸሽቼ ማምለጥ የምችልበት ቦታ የለም፤+ስለ እኔ* የሚያስብ ማንም የለም።  5  ይሖዋ ሆይ፣ እርዳታ ለማግኘት ወደ አንተ እጣራለሁ። ደግሞም “አንተ መጠጊያዬ ነህ፤+በሕያዋን ምድር ያለኸኝ አንተ ብቻ* ነህ” እላለሁ።  6  መንፈሴ እጅግ ተደቁሷልና፣እርዳታ ለማግኘት የማቀርበውን ልመና ስማ። ከእኔ ይልቅ ብርቱ ስለሆኑከሚያሳድዱኝ ሰዎች ታደገኝ።+  7  ስምህን አወድስ ዘንድከእስር ቤት አውጣኝ።* ደግነት ስለምታሳየኝጻድቃን በዙሪያዬ ይሰብሰቡ።

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ጉልበቴ።”
ቃል በቃል “ለእኔ እውቅና የሚሰጥ።”
ወይም “ስለ ነፍሴ።”
ቃል በቃል “በሕያዋን ምድር ድርሻዬ አንተ ነህ።”
ወይም “ነፍሴን ከእስር ቤት አውጣት።”