መዝሙር 104:1-35

  • ድንቅ ለሆኑት የፍጥረት ሥራዎች አምላክን ማወደስ

    • ምድር ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች (5)

    • የወይን ጠጅና ምግብ ሰውን ያስደስታል (15)

    • “ሥራህ ምንኛ ብዙ ነው!” (24)

    • ‘መንፈሳቸውን ስትወስድ ይሞታሉ’ (29)

104  ይሖዋን ላወድስ።*+ ይሖዋ አምላኬ ሆይ፣ አንተ እጅግ ታላቅ ነህ።+ ሞገስንና* ግርማን ለብሰሃል።+  2  ብርሃንን እንደ ልብስ ተጎናጽፈሃል፤+ሰማያትን እንደ ድንኳን መጋረጃ ዘርግተሃል።+  3  የላይኛዎቹን ክፍሎች ተሸካሚዎች ከላይ ባሉት ውኃዎች ላይ* ያኖራል፤+ደመናትን ሠረገላው ያደርጋል፤+በነፋስ ክንፎችም ይሄዳል።+  4  መላእክቱን መናፍስት፣አገልጋዮቹን የሚባላ እሳት ያደርጋል።+  5  ምድርን በመሠረቶቿ ላይ መሠረታት፤+እሷም ለዘላለም ከቦታዋ አትናወጥም።+  6  ጥልቅ ውኃን እንደ ልብስ አለበስካት።+ ውኃዎቹ ከተራሮቹ በላይ ቆሙ።  7  በገሠጽካቸው ጊዜ ሸሹ፤+የነጎድጓድህን ድምፅ ሲሰሙ በድንጋጤ ፈረጠጡ፤  8  ተራሮች ወደ ላይ ወጡ፤+ ሸለቆዎችም ወደ ታች ወረዱ፤ሁሉም ወዳዘጋጀህላቸው ቦታ ሄዱ።  9  ውኃዎቹ አልፈው እንዳይሄዱ፣እንደገናም ምድርን እንዳይሸፍኑ ወሰን አበጀህላቸው።+ 10  ምንጮችን ወደ ሸለቆዎች* ይልካል፤በተራሮች መካከል ይፈስሳሉ። 11  የዱር አራዊት ሁሉ ከዚያ ይጠጣሉ፤የዱር አህዮችም ጥማቸውን ይቆርጣሉ። 12  የሰማይ ወፎች ከእነሱ በላይ ይሰፍራሉ፤በለመለሙ የዛፍ ቅርንጫፎች መካከል ሆነው ይዘምራሉ። 13  ከላይ ካሉት ክፍሎቹ ሆኖ ተራሮችን ያጠጣል።+ በሥራህ ፍሬ ምድር ረካች።+ 14  ሣርን ለከብት፣አትክልትንም ለሰው ልጆች ጥቅም ያበቅላል፤+ይህን የሚያደርገው ምድር እህል እንድታስገኝ ነው፤ 15  እንዲሁም የሰውን ልብ ደስ የሚያሰኝ የወይን ጠጅ፣+ፊትን የሚያበራ ዘይትናየሰውን ልብ የሚያበረታ እህል እንዲገኝ ነው።+ 16  የይሖዋ ዛፎች፣ እሱ የተከላቸው አርዘ ሊባኖሶች፣ውኃ ጠጥተው ይረካሉ፤ 17  በዚያ ወፎች ጎጇቸውን ይሠራሉ። ራዛ*+ በጥድ ዛፎች ላይ ትኖራለች። 18  ረጃጅሞቹ ተራሮች፣ የተራራ ፍየሎች+ መኖሪያ ናቸው፤ቋጥኞቹ የሽኮኮዎች+ መሸሸጊያ ናቸው። 19  ጊዜያትን ለመለየት ጨረቃን ሠራ፤ፀሐይ የምትጠልቅበትን ጊዜ በሚገባ ታውቃለች።+ 20  ጨለማን ታመጣለህ፤ ሌሊትም ይሆናል፤+በዚህ ጊዜ በጫካ የሚኖሩ አራዊት ሁሉ ወጥተው ይንቀሳቀሳሉ። 21  ደቦል አንበሶች አደን ለማግኘት ያገሳሉ፤+ምግባቸውንም ከአምላክ ይሻሉ።+ 22  ፀሐይ ስትወጣ፣ተመልሰው በየጎሬአቸው ይተኛሉ። 23  ሰውም ወደ ሥራው ተሰማርቶእስኪመሽ ድረስ ሲሠራ ይውላል። 24  ይሖዋ ሆይ፣ ሥራህ ምንኛ ብዙ ነው!+ ሁሉንም በጥበብ ሠራህ።+ ምድር በፈጠርካቸው ነገሮች ተሞልታለች። 25  ባሕሩ እጅግ ትልቅና ሰፊ ነው፤በዚያ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ትናንሽም ሆኑ ትላልቅ ሕያዋን ነገሮች ይርመሰመሳሉ።+ 26  በዚያም መርከቦች ይጓዛሉ፤በዚያ እንዲጫወት የፈጠርከው ሌዋታንም*+ በውስጡ ይሄዳል። 27  በወቅቱ ምግባቸውን እንድትሰጣቸው፣ሁሉም አንተን ይጠባበቃሉ።+ 28  አንተ የምትሰጣቸውን ይሰበስባሉ።+ እጅህን ስትከፍት መልካም ነገሮችን ይጠግባሉ።+ 29  ፊትህን ስትሰውር ይታወካሉ። መንፈሳቸውን ከወሰድክ ይሞታሉ፤ ወደ አፈርም ይመለሳሉ።+ 30  መንፈስህን ከላክ ይፈጠራሉ፤+የምድርንም ገጽ ታድሳለህ። 31  የይሖዋ ክብር ለዘላለም ይኖራል። ይሖዋ በሥራው ሐሴት ያደርጋል።+ 32  ምድርን ሲመለከት ትንቀጠቀጣለች፤ተራሮችን ሲነካ ይጨሳሉ።+ 33  በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ለይሖዋ እዘምራለሁ፤+በሕይወት እስካለሁ ድረስ ለአምላኬ የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ።+ 34  ሐሳቤ እሱን የሚያስደስት ይሁን።* እኔም በይሖዋ ሐሴት አደርጋለሁ። 35  ኃጢአተኞች ከምድር ይጠፋሉ፤ክፉዎችም ከእንግዲህ አይገኙም።+ ይሖዋን ላወድስ።* ያህን አወድሱ!*

የግርጌ ማስታወሻዎች

^ ወይም “ክብርንና።”
^ ወይም “ነፍሴ ይሖዋን ታወድስ።”
^ ቃል በቃል “በውኃዎቹ ውስጥ።”
^ ወይም “ደረቅ ወንዞች።”
^ ባለ ረጃጅም እግር ትልቅ አሞራ።
^ “ስለ እሱ የማሰላስለው ነገር ደስ የሚያሰኝ ይሁን” ማለትም ሊሆን ይችላል።
^ ወይም “ነፍሴ ይሖዋን ታወድስ።”
^ ወይም “ሃሌሉያህ!” “ያህ” የይሖዋ ስም አጭር መጠሪያ ነው።