መዝሙር 3:1-8

  • አደጋ ቢኖርም በአምላክ መተማመን

    • “ባላጋራዎቼ እንዲህ የበዙት ለምንድን ነው?” (1)

    • “ማዳን የይሖዋ ነው” (8)

የዳዊት ማህሌት፤* ከልጁ ከአቢሴሎም በሸሸ ጊዜ።+ 3  ይሖዋ ሆይ፣ ጠላቶቼ እንዲህ የበዙት ለምንድን ነው?+ ብዙ ሰዎች በእኔ ላይ የተነሱትስ ለምንድን ነው?+  2  ብዙዎች “አምላክ አያድነውም” እያሉ ስለ እኔ* ይናገራሉ።+ (ሴላ)*  3  ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ግን በዙሪያዬ ያለህ ጋሻ ነህ፤+አንተ ክብሬና+ ራሴን ቀና የምታደርግ ነህ።+  4  ድምፄን ከፍ አድርጌ ይሖዋን እጣራለሁ፤እሱም ከተቀደሰ ተራራው ይመልስልኛል።+ (ሴላ)  5  እተኛለሁ፣ አንቀላፋለሁም፤ይሖዋም ዘወትር ስለሚደግፈኝበሰላም እነቃለሁ።+  6  በየአቅጣጫው የተሰለፉብኝንበአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አልፈራም።+  7  ይሖዋ ሆይ፣ ተነስ! አምላኬ ሆይ፣ አድነኝ!+ የጠላቶቼን ሁሉ መንጋጋ ትመታለህና፤የክፉዎችን ጥርስ ትሰባብራለህ።+  8  ማዳን የይሖዋ ነው።+ በረከትህ በሕዝብህ ላይ ነው። (ሴላ)

የግርጌ ማስታወሻዎች

መንፈሳዊ መዝሙርን ያመለክታል።
ወይም “ስለ ነፍሴ።”