መዝሙር 101:1-8

  • በንጹሕ አቋም የሚመላለስ ገዢ

    • ‘ትዕቢትን አልታገሥም’ (5)

    • ‘ወደ ታማኞች እመለከታለሁ’ (6)

የዳዊት መዝሙር። ማህሌት። 101  ስለ ታማኝ ፍቅርና ስለ ፍትሕ እዘምራለሁ። ይሖዋ ሆይ፣ ለአንተ የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ።  2  በማስተዋልና ነቀፋ በሌለበት መንገድ* እመላለሳለሁ። ወደ እኔ የምትመጣው መቼ ነው? በቤቴ ውስጥ በንጹሕ ልብ* እመላለሳለሁ።+  3  በዓይኖቼ ፊት የማይረባ* ነገር አላኖርም። ከትክክለኛው መንገድ የሚወጡ ሰዎች የሚያደርጓቸውን ነገሮች እጠላለሁ፤+ከእነሱ ጋር የሚያገናኘኝ ምንም ጉዳይ የለም።*  4  ጠማማ ልብ ከእኔ የራቀ ነው፤ምንም ዓይነት ክፉ ነገር አልቀበልም።*  5  የባልንጀራውን ስም በስውር የሚያጠፋን ሰው፣+ጸጥ አሰኘዋለሁ።* ትዕቢተኛ ዓይንና እብሪተኛ ልብ ያለውን ሰው፣አልታገሠውም።  6  ከእኔ ጋር እንዲኖሩበምድሪቱ ወዳሉ ታማኞች እመለከታለሁ። ነቀፋ በሌለበት መንገድ* የሚመላለስ ሰው እኔን ያገለግለኛል።  7  አታላይ የሆነ ሰው በቤቴ አይኖርም፤ውሸት የሚናገር ሰው በፊቴ* አይቆምም።  8  በምድሪቱ ላይ የሚገኙትን ክፉ ሰዎች ሁሉ በየማለዳው ጸጥ አሰኛለሁ፤*ክፉ አድራጊዎችን ሁሉ ከይሖዋ ከተማ አስወግዳለሁ።+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “በንጹሕ አቋም።”
መዝ 7:8 ላይ የሚገኘውን የግርጌ ማስታወሻ ተመልከት።
ወይም “ከንቱ።”
ወይም “ተግባራቸው ከእኔ ጋር አይጣበቅም።”
ቃል በቃል “አላውቅም።”
ወይም “አጠፋዋለሁ።”
ወይም “በንጹሕ አቋም።”
ቃል በቃል “በዓይኖቼ ፊት።”
ወይም “አጠፋቸዋለሁ።”