መዝሙር 116:1-19
116 ይሖዋ ድምፄን፣እርዳታ ለማግኘት የማቀርበውን ልመና ስለሚሰማ እወደዋለሁ።*+
2 ጆሮውን ወደ እኔ ያዘነብላልና፣*+በሕይወት እስካለሁ ድረስ* እሱን እጣራለሁ።
3 የሞት ገመዶች ተተበተቡብኝ፤መቃብር ያዘኝ።*+
በጭንቀትና በሐዘን ተዋጥኩ።+
4 እኔ ግን የይሖዋን ስም ጠራሁ፦+
“ይሖዋ ሆይ፣ ታደገኝ!”*
5 ይሖዋ ሩኅሩኅና* ጻድቅ ነው፤+አምላካችን መሐሪ ነው።+
6 ይሖዋ ተሞክሮ የሌላቸውን ይጠብቃል።+
ተስፋ ቆርጬ ነበር፤ እሱ ግን አዳነኝ።
7 ነፍሴ* ዳግመኛ እረፍት ታግኝ፤ይሖዋ ደግነት አሳይቶኛልና።
8 እኔን* ከሞት፣ ዓይኔን ከእንባ፣እግሬንም ከእንቅፋት ታድገሃል።+
9 በሕያዋን ምድር በይሖዋ ፊት እሄዳለሁ።
10 አመንኩ ስለዚህም ተናገርኩ፤+እጅግ ተጎሳቁዬ ነበር።
11 በጣም ደንግጬ
“ሰው ሁሉ ውሸታም ነው”+ አልኩ።
12 ላደረገልኝ መልካም ነገር ሁሉለይሖዋ ምን እመልስለታለሁ?
13 የማዳንን ጽዋ አነሳለሁ፤የይሖዋንም ስም እጠራለሁ።
14 በሕዝቡ ሁሉ ፊትስእለቴን ለይሖዋ እፈጽማለሁ።+
15 የታማኝ አገልጋዮቹ ሞትበይሖዋ ዓይን ከባድ ነገር* ነው።+
16 ይሖዋ ሆይ፣እኔ አገልጋይህ ስለሆንኩ እለምንሃለሁ።
እኔ የሴት ባሪያህ ልጅ፣ አገልጋይህ ነኝ።
አንተ ከእስራቴ ነፃ አውጥተኸኛል።+
17 ለአንተ የምስጋና መሥዋዕት አቀርባለሁ፤+የይሖዋን ስም እጠራለሁ።
18 በሕዝቡ ሁሉ ፊት፣ስእለቴን ለይሖዋ እፈጽማለሁ፤+
19 በይሖዋ ቤት ቅጥር ግቢዎች፣+በኢየሩሳሌም መካከል ስእለቴን አቀርባለሁ።
ያህን አወድሱ!*+
የግርጌ ማስታወሻዎች
^ “ይሖዋ ስለሚሰማ ውስጤ በፍቅር ይሞላል” ማለትም ሊሆን ይችላል።
^ ወይም “ጎንበስ ብሎ ይሰማኛልና።”
^ ቃል በቃል “በቀኖቼ።”
^ ቃል በቃል “የሲኦል ጭንቅ አገኘኝ።”
^ ወይም “ነፍሴን ታደግ።”
^ ወይም “ቸርና።”
^ የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
^ ወይም “ነፍሴን።”
^ ቃል በቃል “ክቡር።”
^ ወይም “ሃሌሉያህ!” “ያህ” የይሖዋ ስም አጭር መጠሪያ ነው።