መዝሙር 134:1-3

  • በሌሊት አምላክን ማወደስ

    • “እጆቻችሁን በቅድስና ወደ ላይ አንሱ” (2)

ወደ ላይ የመውጣት መዝሙር። 134  በሌሊት በይሖዋ ቤት የምታገለግሉ፣+እናንተ የይሖዋ አገልጋዮች ሁሉ፣ይሖዋን አወድሱ።+   እጆቻችሁን በቅድስና* ወደ ላይ አንሱ፤+ይሖዋንም አወድሱ።   ሰማይንና ምድርን የሠራው ይሖዋ፣ከጽዮን ይባርክህ።

የግርጌ ማስታወሻዎች

“በመቅደሱ ውስጥ” ማለትም ሊሆን ይችላል።