መዝሙር 131:1-3

  • “ጡት እንደጣለ ሕፃን ረካሁ”

    • ‘ታላላቅ ነገሮችን አልመኝም’ (1)

ወደ ላይ የመውጣት መዝሙር። የዳዊት መዝሙር። 131  ይሖዋ ሆይ፣ ልቤ አይኩራራም፤ዓይኖቼም አይታበዩም፤+እጅግ ታላላቅ ነገሮችን ወይምከአቅሜ በላይ የሆኑ ነገሮችን አልመኝም።+   ይልቁንም እናቱ ላይ እንደተቀመጠ ጡት የጣለ ሕፃንነፍሴን አረጋጋኋት፤* ደግሞም ጸጥ አሰኘኋት።+ጡት እንደጣለ ሕፃን ረካሁ።*   እስራኤል ከአሁን ጀምሮ ለዘላለምይሖዋን በትዕግሥት ይጠባበቅ።+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ራሴን አረጋጋሁ።” የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ወይም “ነፍሴ ጡት እንደጣለ ሕፃን ረካች።”