መዝሙር 37:1-40

 • በይሖዋ የሚታመኑ ይበለጽጋሉ

  • “በክፉዎች አትበሳጭ” (1)

  • “በይሖዋ ሐሴት አድርግ” (4)

  • “መንገድህን ለይሖዋ አደራ ስጥ” (5)

  • ‘የዋሆች ምድርን ይወርሳሉ’ (11)

  • ጻድቅ እህል ሲለምን አላየሁም (25)

  • ጻድቃን በምድር ላይ ለዘላለም ይኖራሉ (29)

የዳዊት መዝሙር። א [አሌፍ] 37  በክፉዎች አትበሳጭ፤*ወይም በክፉ አድራጊዎች አትቅና።+   እንደ ሣር በፍጥነት ይደርቃሉ፤+እንደለመለመ ተክልም ይጠወልጋሉ። ב [ቤት]   በይሖዋ ታመን፤ መልካም የሆነውንም አድርግ፤+በምድር ላይ ኑር፤ ለሰዎችም ታማኝ ሁን።+   በይሖዋ ሐሴት አድርግ፤*እሱም የልብህን መሻት ይሰጥሃል። ג [ጊሜል]   መንገድህን ለይሖዋ አደራ ስጥ፤*+በእሱ ታመን፤ እሱም ለአንተ ሲል እርምጃ ይወስዳል።+   ጽድቅህን እንደ ንጋት ብርሃን፣የአንተንም ፍትሕ እንደ ቀትር ፀሐይ ያበራዋል። ד [ዳሌት]   በይሖዋ ፊት ዝም በል፤+እሱንም በተስፋ* ተጠባበቅ። የጠነሰሰውን ሴራበተሳካ ሁኔታ እየፈጸመ ባለ ሰው አትበሳጭ።+ ה []   ከቁጣ ተቆጠብ፤ ንዴትንም ተው፤+ተበሳጭተህ ክፉ ነገር አትሥራ።*   ክፉ አድራጊዎች ይጠፋሉና፤+ይሖዋን ተስፋ የሚያደርጉ ግን ምድርን ይወርሳሉ።+ ו [ዋው] 10  ለጥቂት ጊዜ ነው እንጂ ክፉዎች አይኖሩም፤+በቀድሞ ቦታቸው ትፈልጋቸዋለህ፤እነሱ ግን በዚያ አይገኙም።+ 11  የዋሆች ግን ምድርን ይወርሳሉ፤+በብዙ ሰላምም እጅግ ደስ ይላቸዋል።+ ז [ዛየን] 12  ክፉ ሰው በጻድቁ ላይ ያሴራል፤+በእሱ ላይ ጥርሱን ያፋጫል። 13  ይሖዋ ግን ይስቅበታል፤የሚጠፋበት ቀን እንደሚደርስ ያውቃልና።+ ח [ኼት] 14  ክፉዎች የተጨቆነውንና ድሃውን ለመጣል፣እንዲሁም ቀና የሆነውን መንገድ የሚከተሉትን ለማረድሰይፋቸውን ይመዛሉ፤ ደጋናቸውንም ይወጥራሉ። 15  ሆኖም ሰይፋቸው የገዛ ልባቸውን ይወጋል፤+ደጋኖቻቸው ይሰበራሉ። ט [ቴት] 16  ብዙ ክፉ ሰዎች ካላቸው የተትረፈረፈ ሀብት ይልቅጻድቅ ሰው ያለው ጥቂት ነገር ይሻላል።+ 17  የክፉዎች ክንድ ይሰበራልና፤ይሖዋ ግን ጻድቃንን ይደግፋል። י [ዮድ] 18  ይሖዋ ነቀፋ የሌለባቸውን ሰዎች የሕይወት ጎዳና* ያውቃል፤ርስታቸውም ለዘላለም ይኖራል።+ 19  በአደጋ ወቅት ለኀፍረት አይዳረጉም፤በረሃብ ዘመን የተትረፈረፈ ምግብ ይኖራቸዋል። כ [ካፍ] 20  ክፉዎች ግን ይጠፋሉ፤+የይሖዋ ጠላቶች እንደ መስክ ውበት ይከስማሉ፤እንደ ጭስ ይበናሉ። ל [ላሜድ] 21  ክፉ ሰው ይበደራል፤ መልሶም አይከፍልም፤ጻድቅ ሰው ግን ለጋስ ነው፤* ደግሞም ይሰጣል።+ 22  አምላክ የባረካቸው ምድርን ይወርሳሉ፤እሱ የረገማቸው ግን ይጠፋሉ።+ מ [ሜም] 23  ይሖዋ በሰው መንገድ ደስ ሲሰኝ፣+አካሄዱን ይመራለታል።*+ 24  ቢወድቅም እንኳ አይዘረርም፤+ይሖዋ እጁን ይዞ* ይደግፈዋልና።+ נ [ኑን] 25  በአንድ ወቅት ወጣት ነበርኩ፤ አሁን ግን አርጅቻለሁ፤ይሁንና ጻድቅ ሰው ሲጣል፣+ልጆቹም ምግብ* ሲለምኑ አላየሁም።+ 26  ሁልጊዜ ሳይሰስት ያበድራል፤+ልጆቹም በረከት ያገኛሉ። ס [ሳሜኽ] 27  ከክፉ ራቅ፤ መልካሙንም አድርግ፤+ለዘላለምም ትኖራለህ። 28  ይሖዋ ፍትሕን ይወዳልና፤ታማኝ አገልጋዮቹንም አይተዋቸውም።+ ע [አይን] ምንጊዜም ጥበቃ ያገኛሉ፤+የክፉዎች ዘር ግን ይጠፋል።+ 29  ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ፤+በእሷም ላይ ለዘላለም ይኖራሉ።+ פ [] 30  የጻድቅ አፍ ጥበብን ይናገራል፤*ምላሱም ስለ ፍትሕ ያወራል።+ 31  የአምላኩ ሕግ በልቡ አለ፤+በሚሄድበት ጊዜም እግሮቹ አይብረከረኩም።+ צ [ጻዴ] 32  ክፉ ሰው ጻድቁን ለመግደልበዓይነ ቁራኛ ይከታተለዋል። 33  ይሖዋ ግን በክፉው እጅ አይጥለውም፤+ወይም ለፍርድ በሚቀርብበት ጊዜ ጥፋት አያገኝበትም።+ ק [ኮፍ] 34  ይሖዋን ተስፋ አድርግ፤ መንገዱንም ተከተል፤እሱም ከፍ ከፍ ያደርግሃል፤ ምድርንም ትወርሳለህ። ክፉዎች ሲጠፉ+ ታያለህ።+ ר [ረሽ] 35  ጨካኝ የሆነውን ክፉ ሰው፣በበቀለበት መሬት ላይ እንደለመለመ ዛፍ ተንሰራፍቶ አየሁት።+ 36  ይሁንና ሕይወቱ በድንገት አለፈ፤ በቦታውም አልነበረም፤+አጥብቄ ፈለግኩት፤ ላገኘው ግን አልቻልኩም።+ ש [ሺን] 37  ነቀፋ የሌለበትን* ሰው ልብ በል፤ቀና የሆነውንም ሰው+ በትኩረት ተመልከት፤የዚህ ሰው የወደፊት ሕይወት ሰላማዊ ይሆናልና።+ 38  ኃጢአተኞች ሁሉ ግን ይጠፋሉ፤ክፉዎች ምንም ተስፋ አይኖራቸውም።+ ת [ታው] 39  ጻድቃን መዳን የሚያገኙት ከይሖዋ ነው፤+በጭንቅ ጊዜ መሸሸጊያቸው እሱ ነው።+ 40  ይሖዋ ይረዳቸዋል፤ ይታደጋቸዋልም።+ እሱን መጠጊያ ስላደረጉ፣ከክፉዎች ይታደጋቸዋል፤ ደግሞም ያድናቸዋል።+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ቱግ አትበል።”
ወይም “በይሖዋ እጅግ ደስ ይበልህ።”
ወይም “ሸክምህን ወደ ይሖዋ አንከባለው።”
ወይም “በትዕግሥት።”
“ጉዳት ላይ ሊጥልህ ስለሚችል አትበሳጭ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ቃል በቃል “ነቀፋ የሌለባቸውን ሰዎች ቀናት።”
ወይም “ቸርነት ያደርጋል።”
ወይም “አካሄዱን ያጸናለታል።”
ወይም “በእጁ።”
ቃል በቃል “ዳቦ።”
ወይም “በለሆሳስ ይናገራል።”
ወይም “ንጹሕ አቋሙን የሚጠብቅን።”