መዝሙር 67:1-7

  • የምድር ዳርቻዎች አምላክን ይፈራሉ

    • የአምላክ መንገድ ይታወቃል (2)

    • “ሕዝቦች ሁሉ ያወድሱህ” (3, 5)

    • “አምላክ ይባርከናል” (6, 7)

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ በባለ አውታር መሣሪያዎች የሚታጀብ። ማህሌት። መዝሙር። 67  አምላክ ሞገስ ያሳየናል፤ ደግሞም ይባርከናል፤ፊቱን በእኛ ላይ ያበራል፤+ (ሴላ)   ይህም መንገድህ በምድር ሁሉ ላይ፣+የማዳን ሥራህም በብሔራት ሁሉ መካከል እንዲታወቅ ነው።+   አምላክ ሆይ፣ ሕዝቦች ያወድሱህ፤አዎ፣ ሕዝቦች ሁሉ ያወድሱህ።   ብሔራት ሐሴት ያድርጉ፤ እልልም ይበሉ፤+በሕዝቦች ላይ በትክክል ትፈርዳለህና።+ የምድርን ብሔራት ትመራቸዋለህ። (ሴላ)   አምላክ ሆይ፣ ሕዝቦች ያወድሱህ፤ሕዝቦች ሁሉ ያወድሱህ።   ምድር ፍሬዋን ትሰጣለች፤+አምላክ፣ አዎ፣ አምላካችን ይባርከናል።+   አምላክ ይባርከናል፤የምድር ዳርቻዎችም ሁሉ ይፈሩታል።*+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ያከብሩታል።”