መዝሙር 17:1-15

  • ጥበቃ ለማግኘት የቀረበ ጸሎት

    • “ልቤን መረመርክ” (3)

    • “በክንፎችህ ጥላ ሰውረኝ” (8)

የዳዊት ጸሎት። 17  ይሖዋ ሆይ፣ ፍትሕ ለማግኘት የማቀርበውን ልመና ስማ፤እርዳታ ለማግኘት የማሰማውን ጩኸት በጥሞና አዳምጥ፤ያለምንም ማታለል ያቀረብኩትን ጸሎት ስማ።+  2  ለእኔ ስትል ፍትሐዊ ውሳኔ አድርግ፤+ዓይኖችህ ትክክለኛ የሆነውን ነገር ይዩ።  3  ልቤን መረመርክ፤ በሌሊት በሚገባ አጤንከኝ፤+ደግሞም አጠራኸኝ፤+አንዳች መጥፎ ነገር እንዳላሰብኩ ታውቃለህ፤አንደበቴም አልበደለም።  4  የሰዎችን ሥራ በተመለከተ ደግሞ፣የከንፈርህን ቃል በማክበር ከዘራፊዎች መንገድ ርቄአለሁ።+  5  እግሮቼ እንዳይደነቃቀፉ፣አረማመዴ በመንገድህ ላይ ይጽና።+  6  አምላክ ሆይ፣ መልስ ስለምትሰጠኝ አንተን እጣራለሁ።+ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል።* ቃሌን ስማ።+  7  በቀኝ እጅህ እንድትጠብቃቸው የሚሹትን፣በአንተ ላይ ከሚያምፁ ሰዎች የምታድን ሆይ፣ታማኝ ፍቅርህን ድንቅ በሆነ መንገድ አሳይ።+  8  እንደ ዓይንህ ብሌን ጠብቀኝ፤+በክንፎችህ ጥላ ሰውረኝ።+  9  ጥቃት ከሚሰነዝሩብኝ ክፉዎች፣ከሚከቡኝና ሊገድሉኝ ከሚፈልጉ ጠላቶቼ* ጠብቀኝ።+ 10  ደንታ ቢሶች ሆነዋል፤*በአፋቸው በእብሪት ይናገራሉ፤ 11  መፈናፈኛ አሳጡን፤+እኛን መጣል* የሚችሉበትን አጋጣሚ ነቅተው ይጠባበቃሉ። 12  እያንዳንዳቸው ያደነውን ለመዘነጣጠል እንደሚጓጓ አንበሳ፣በስውር እንደሚያደባ ደቦል አንበሳ ናቸው። 13  ይሖዋ ሆይ፣ ተነስተህ ፊት ለፊት ግጠመው፤+ ደግሞም ጣለው፤በሰይፍህ ከክፉው ሰው ታደገኝ፤* 14  ይሖዋ ሆይ፣ ከዚህ ዓለም* ሰዎች በእጅህ ታደገኝ፤እነዚህ ሰዎች ድርሻቸው አሁን ያለው ሕይወት ነው፤+አንተ በሰጠሃቸው መልካም ነገሮች አጥግበሃቸዋል፤+ደግሞም ለብዙ ወንዶች ልጆቻቸው ርስት ያስተላልፋሉ። 15  እኔ ግን ፊትህን በጽድቅ አያለሁ፤በምነቃበት ጊዜ አንተን በማየት እደሰታለሁ።+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ጎንበስ ብለህ ስማኝ።”
ወይም “በነፍስ ላይ ከተነሱ ጠላቶቼ።”
ወይም “በገዛ ራሳቸው ስብ ተሸፍነዋል።”
ወይም “መሬት ላይ መጣል።”
ወይም “ነፍሴን ታደጋት።”
ወይም “ሥርዓት።”