መዝሙር 128:1-6

  • ይሖዋን በመፍራት የሚገኝ ደስታ

    • እንደሚያፈራ ወይን የሆነች ሚስት (3)

    • “የኢየሩሳሌምን ብልጽግና ለማየት ያብቃህ” (5)

ወደ ላይ የመውጣት መዝሙር። 128  ይሖዋን የሚፈሩ፣በመንገዱም የሚሄዱ ሁሉ ደስተኞች ናቸው።+  2  በእጅህ ደክመህ ያፈራኸውን ትበላለህ። ደስተኛ ትሆናለህ፤ ደግሞም ትበለጽጋለህ።+  3  ሚስትህ በቤትህ ውስጥ፣ ፍሬ እንደሚያፈራ ወይን ትሆናለች፤+ወንዶች ልጆችህ በማዕድህ ዙሪያ እንደ ወይራ ዛፍ ቡቃያዎች ይሆናሉ።  4  እነሆ፣ ይሖዋን የሚፈራ ሰውእንደዚህ የተባረከ ይሆናል።+  5  ይሖዋ ከጽዮን ይባርክሃል። በሕይወት ዘመንህ ሁሉ የኢየሩሳሌምን ብልጽግና ለማየት ያብቃህ፤+  6  ደግሞም የልጅ ልጅ ለማየት ያብቃህ። በእስራኤል ሰላም ይስፈን።

የግርጌ ማስታወሻዎች