መዝሙር 20:1-9

  • አምላክ የቀባውን ንጉሥ ያድናል

    • አንዳንዶች በሠረገሎችና በፈረሶች ይታመናሉ፤ ‘እኛ ግን የይሖዋን ስም እንጠራለን’ (7)

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የዳዊት ማህሌት። 20  በጭንቀት ቀን ይሖዋ ይስማህ። የያዕቆብ አምላክ ስም ይጠብቅህ።+  2  ከቅዱሱ ስፍራ እርዳታ ይላክልህ፤+ከጽዮንም ደግፎ ይያዝህ።+  3  በስጦታ የምታቀርበውን መባ ሁሉ ያስብልህ፤የሚቃጠል መባህን በሞገስ ዓይን* ይቀበልህ። (ሴላ)  4  የልብህን ፍላጎት ያሟላልህ፤+ዕቅድህንም* ሁሉ ያሳካልህ።  5  በማዳን ሥራህ በደስታ እልል እንላለን፤+በአምላካችን ስም ዓርማችንን ወደ ላይ ከፍ እናደርጋለን።+ ይሖዋ የለመንከውን ሁሉ ይፈጽምልህ።  6  ይሖዋ የቀባውን እንደሚያድን አሁን አወቅኩ።+ በቀኝ እጁ በሚያከናውነው ታላቅ የማዳን ሥራ፣*+ቅዱስ ከሆኑት ሰማያቱ ይመልስለታል።  7  አንዳንዶች በሠረገሎች፣ ሌሎች ደግሞ በፈረሶች ይታመናሉ፤+እኛ ግን የአምላካችንን የይሖዋን ስም እንጠራለን።+  8  እነሱ ተዝለፍልፈው ወድቀዋል፤እኛ ግን ተነስተን ቀጥ ብለን ቆመናል።+  9  ይሖዋ ሆይ፣ ንጉሡን አድን!+ እርዳታ ለማግኘት በተጣራን ቀን ይመልስልናል።+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ቃል በቃል “እንደ ስብ ቆጥሮ።”
ወይም “ምክርህንም።”
ወይም “በሚቀዳጀው ታላቅ ድል።”