መዝሙር 50:1-23

  • አምላክ በሕዝቡ ላይ ይፈርዳል

    • በመሥዋዕት አማካኝነት ከአምላክ ጋር የሚደረግ ቃል ኪዳን (5)

    • “አምላክ ራሱ ፈራጅ ነው” (6)

    • እንስሳት ሁሉ የአምላክ ናቸው (10, 11)

    • አምላክ ክፉዎችን ያጋልጣል (16-21)

የአሳፍ+ ማህሌት። 50  የአማልክት አምላክ የሆነው ይሖዋ+ ተናግሯል፤ከፀሐይ መውጫ አንስቶ እስከ መግቢያው* ድረስምድርን ይጠራል።   በውበቷ ፍጹም ከሆነችው ከጽዮን፣+ አምላክ ያበራል።   አምላካችን ይመጣል፤ ፈጽሞም ዝም ሊል አይችልም።+ በፊቱ የሚባላ እሳት አለ፤+በዙሪያውም ሁሉ ኃይለኛ አውሎ ነፋስ ይነፍሳል።+   በሕዝቡ ላይ ለመፍረድ፣+በላይ ያሉትን ሰማያትና ምድርን ይጠራል፤+   “በመሥዋዕት አማካኝነት ከእኔ ጋር ቃል ኪዳን የሚያደርጉትን፣+ታማኝ አገልጋዮቼን ወደ እኔ ሰብስቡ” ይላል።   ሰማያት ጽድቁን ያውጃሉ፤አምላክ ራሱ ፈራጅ ነውና።+ (ሴላ)   “ሕዝቤ ሆይ፣ ስማ፤ እኔም እናገራለሁ፤እስራኤል ሆይ፣ በአንተ ላይ እመሠክርብሃለሁ።+ እኔ አምላክ፣ አዎ አምላክህ ነኝ።+   በመሥዋዕቶችህም ሆነዘወትር በፊቴ ባሉት የሚቃጠሉ መባዎችህ የተነሳ አልወቅስህም።+   ከቤትህ ኮርማ፣ከጉረኖህም ፍየሎች* መውሰድ አያስፈልገኝም።+ 10  በጫካ ውስጥ ያሉ የዱር እንስሳት ሁሉ፣በሺህ ተራሮች ላይ ያሉ አራዊትም እንኳ የእኔ ናቸውና።+ 11  በተራሮች ላይ የሚኖሩትን ወፎች ሁሉ አውቃለሁ፤+በመስክ ያሉ ስፍር ቁጥር የሌላቸው እንስሳት የእኔ ናቸው። 12  ብራብ እንኳ ለአንተ አልነግርህም፤ፍሬያማ የሆነችው ምድርና በውስጧ ያለው ሁሉ የእኔ ነውና።+ 13  የኮርማዎችን ሥጋ እበላለሁ?የፍየሎችንስ ደም እጠጣለሁ?+ 14  ምስጋናን ለአምላክ መሥዋዕት አድርገህ አቅርብ፤+ስእለትህንም ለልዑሉ አምላክ ስጥ፤+ 15  በጭንቅ ቀን ጥራኝ።+ እኔ እታደግሃለሁ፤ አንተም ታወድሰኛለህ።”+ 16  ክፉውን ግን አምላክ እንዲህ ይለዋል፦ “ስለ ሥርዓቴ ለማውራት፣ወይም ደግሞ ስለ ቃል ኪዳኔ ለመናገር ምን መብት አለህ?+ 17  ተግሣጼን* ትጠላለህና፤ለቃሌም ጀርባህን ትሰጣለህ።*+ 18  ሌባ ስታይ ትደግፈዋለህ፤*+ከአመንዝሮችም ጋር ትወዳጃለህ። 19  አንደበትህን ክፉ ወሬ ለመንዛት ትጠቀምበታለህ፤ማታለያም ከምላስህ አይጠፋም።+ 20  ከሌሎች ጋር ተቀምጠህ ወንድምህን ታማለህ፤+የገዛ እናትህን ልጅ ድክመት ታወራለህ።* 21  እነዚህን ሁሉ ነገሮች ስታደርግ፣ ዝም አልኩ፤በመሆኑም እንደ አንተ የምሆን መስሎህ ነበር። አሁን ግን እወቅስሃለሁ፤ከአንተ ጋር ያለኝንም ሙግት አሳውቃለሁ።+ 22  እናንተ አምላክን የምትረሱ፣ እባካችሁ ይህን ልብ በሉ፤+አለዚያ ብትንትናችሁን አወጣለሁ፤ የሚታደጋችሁም አይኖርም። 23  ምስጋናን መሥዋዕት አድርጎ የሚያቀርብልኝ ያከብረኛል፤+ደግሞም ትክክለኛውን መንገድ በጥብቅ የሚከተልን ሰው፣የአምላክን ማዳን እንዲያይ አደርገዋለሁ።”+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ።”
ቃል በቃል “አውራ ፍየሎች።”
ቃል በቃል “ቃሌንም ወደ ኋላህ ትጥላለህ።”
ወይም “መመሪያዬን፤ ትምህርቴን።”
“ከእሱ ጋር ትተባበራለህ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “ስም ታጠፋለህ።”