መዝሙር 132:1-18

  • ዳዊትና ጽዮን ተመረጡ

    • “የቀባኸውን ሰው ገሸሽ አታድርግ” (10)

    • ካህናቷ መዳንን ይለብሳሉ (16)

ወደ ላይ የመውጣት መዝሙር። 132  ይሖዋ ሆይ፣ ዳዊትን፣የደረሰበትንም መከራ ሁሉ አስታውስ፤+   ለይሖዋ እንዴት እንደማለ፣ኃያል ለሆነው ለያዕቆብ አምላክ እንዴት እንደተሳለ አስብ፦+   “ወደ ድንኳኔ፣ ወደ ቤቴ አልገባም።+ ወደ መኝታዬ፣ ወደ አልጋዬ አልወጣም፤   ዓይኖቼ እንዲያንቀላፉ፣ሽፋሽፍቶቼም እንዲያሸልቡ አልፈቅድም፤   ይህም ለይሖዋ ስፍራ፣ኃያል ለሆነው የያዕቆብ አምላክም ያማረ መኖሪያ እስከማገኝ ድረስ ነው።”+   እነሆ፣ በኤፍራታ+ ስለ እሷ ሰማን፤በጫካ በተሞላው ምድር አገኘናት።+   ወደ መኖሪያው እንግባ፤+በእግሩ ማሳረፊያ ፊት እንስገድ።+   ይሖዋ ሆይ፣ ተነስ፤አንተና የብርታትህ ታቦት፣+ ወደ ማረፊያ ስፍራህ ሂዱ።+   ካህናትህ ጽድቅን ይልበሱ፤ታማኝ አገልጋዮችህም እልል ይበሉ። 10  ለአገልጋይህ ለዳዊት ስትል፣የቀባኸውን ሰው ገሸሽ አታድርግ።+ 11  ይሖዋ ለዳዊት ምሏል፤የገባውን ቃል ፈጽሞ አያጥፍም፦ “ከዘሮችህ መካከል አንዱን*በዙፋንህ ላይ አስቀምጣለሁ።+ 12  ወንዶች ልጆችህ ቃል ኪዳኔንናየማስተምራቸውን ማሳሰቢያዎች ቢጠብቁ፣+የእነሱም ልጆችለዘላለም በዙፋንህ ላይ ይቀመጣሉ።”+ 13  ይሖዋ ጽዮንን መርጧታልና፤+የራሱ መኖሪያ እንድትሆን ፈልጓል፤+ እንዲህም ብሏል፦ 14  “ይህች ለዘላለም ማረፊያ ስፍራዬ ነች፤በእሷ እኖራለሁ፤+ ይህ ምኞቴ ነውና። 15  የተትረፈረፈ የምግብ አቅርቦት እንዲኖራት በማድረግ እባርካታለሁ፤ድሆቿን እህል አጠግባለሁ።+ 16  ካህናቷ መዳንን እንዲለብሱ አደርጋለሁ፤+ታማኝ ሕዝቦቿም እልል ይላሉ።+ 17  በዚያ የዳዊትን ብርታት እጨምራለሁ።* ለቀባሁት አገልጋዬ መብራት አዘጋጅቻለሁ።+ 18  ጠላቶቹን ኀፍረት አከናንባለሁ፤በራሱ ላይ ያለው አክሊል* ግን ያብባል።”+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ቃል በቃል “ከማህፀንህ ፍሬ (አንዱን)።”
ቃል በቃል “የዳዊትን ቀንድ አበቅላለሁ።”
ወይም “ዘውድ።”