መዝሙር 43:1-5

  • ፈራጅ የሆነው አምላክ ይታደጋል

    • “ብርሃንህንና እውነትህን ላክ” (3)

    • “ተስፋ የምቆርጠው ለምንድን ነው?” (5)

    • “አምላክን በትዕግሥት እጠባበቃለሁ” (5)

43  አምላክ ሆይ፣ ፍረድልኝ፤+ከከዳተኛ ብሔር ጋር ያለብኝን ሙግት አንተ ተሟገትልኝ።+ አታላይና ዓመፀኛ ከሆነ ሰው ታደገኝ።   አንተ አምላኬና ምሽጌ ነህና።+ ለምን ተውከኝ? ጠላቴ ከሚያደርስብኝ ጭቆና የተነሳ ለምን አዝኜ ልመላለስ?+   ብርሃንህንና እውነትህን ላክ።+ እነሱ ይምሩኝ፤+ወደተቀደሰው ተራራህና ወደ ታላቁ የማደሪያ ድንኳንህ ይውሰዱኝ።+   ከዚያም ወደ አምላክ መሠዊያ፣+እጅግ ሐሴት ወደማደርግበት አምላክ እመጣለሁ። ደግሞም አምላክ ሆይ፣ አምላኬ፣ በበገና አወድስሃለሁ።+   ተስፋ የምቆርጠው* ለምንድን ነው? ውስጤ የሚረበሸው ለምንድን ነው? አምላክን በትዕግሥት እጠባበቃለሁ፤+እሱን እንደ ታላቅ አዳኜና አምላኬ አድርጌ ገና አወድሰዋለሁና።+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ነፍሴ ተስፋ የምትቆርጠው።”