መዝሙር 10:1-18

  • ይሖዋ ምስኪኑን ይረዳል

    • ክፉ ሰው በትዕቢት “አምላክ የለም” ይላል (4)

    • ምስኪኑ ወደ ይሖዋ ይጮኻል (14)

    • “ይሖዋ ለዘላለም ንጉሥ ነው” (16)

ל [ላሜድ] 10  ይሖዋ ሆይ፣ ርቀህ የምትቆመው ለምንድን ነው? በመከራ ጊዜ ራስህን የምትሰውረው ለምንድን ነው?+   ክፉ ሰው በእብሪት ተነሳስቶ ምስኪኑን ያሳድዳል፤+ይሁንና በወጠነው ሴራ ይያዛል።+   ክፉው ሰው በራስ ወዳድነት ምኞቱ ይኩራራልና፤*+ስግብግብ የሆነውንም ሰው ይባርካል፤*נ [ኑን] ይሖዋንም ያቃልላል።   ክፉው ሰው ከትዕቢቱ የተነሳ ምንም ምርምር አያደርግም፤“አምላክ የለም” ብሎ ያስባል።+   መንገዱ ሁልጊዜ የተሳካ ነው፤+ሆኖም ፍርድህ እሱ ሊገነዘበው ከሚችለው በላይ ነው፤+በጠላቶቹ ሁሉ ላይ ያፌዛል።*   በልቡ እንዲህ ይላል፦ “ፈጽሞ አልናወጥም፤*ከትውልድ እስከ ትውልድምንም መከራ አይደርስብኝም።”+ פ []   አፉ በእርግማን፣ በውሸትና በዛቻ የተሞላ ነው፤+ከምላሱ ሥር ችግርና ጉዳት የሚያስከትል ነገር አለ።+   በመንደሮቹ አጠገብ አድብቶ ይጠብቃል፤ከተደበቀበት ቦታ ወጥቶ ንጹሑን ሰው ይገድላል።+ ע [አይን] ዓይኖቹ ያልታደለውን ሰለባ ይጠባበቃሉ።+   በጎሬው ውስጥ እንዳለ* አንበሳ በተደበቀበት ቦታ አድፍጦ ይጠብቃል።+ ምስኪኑን ሰው ለመያዝ ይጠባበቃል። ምስኪኑን ሰው መረቡ ውስጥ አስገብቶ ይይዘዋል።+ 10  ሰለባው ይደቅቃል፤ ደግሞም ይወድቃል፤ያልታደሉ ሰዎች መዳፉ ውስጥ ይወድቃሉ። 11  በልቡ እንዲህ ይላል፦ “አምላክ ረስቷል።+ ፊቱን አዙሯል። ፈጽሞ ልብ አይልም።”+ ק [ኮፍ] 12  ይሖዋ ሆይ፣ ተነስ።+ አምላክ ሆይ፣ እጅህን አንሳ።+ ምስኪኖችን አትርሳ።+ 13  ክፉው ሰው አምላክን ያቃለለው ለምንድን ነው? በልቡ “ተጠያቂ አታደርገኝም” ይላል። ר [ረሽ] 14  አንተ ግን ችግርንና መከራን ትመለከታለህ። ደግሞም አይተህ እርምጃ ትወስዳለህ።+ ያልታደለው ሰለባ ወደ አንተ ይጮኻል፤+አንተ አባት ለሌለው ልጅ* ረዳቱ ነህ።+ ש [ሺን] 15  ክፉና መጥፎ የሆነውን ሰው ክንድ ስበር፤+ከዚያ በኋላ ክፋቱን በምትፈልግበት ጊዜጨርሶ አታገኘውም። 16  ይሖዋ ለዘላለም ንጉሥ ነው።+ ብሔራት ከምድር ጠፍተዋል።+ ת [ታው] 17  ይሖዋ ሆይ፣ የዋሆች የሚያቀርቡትን ልመና ግን ትሰማለህ።+ ልባቸውን ታጸናለህ፤+ ደግሞም ትኩረት ትሰጣቸዋለህ።+ 18  በምድር ላይ ያለ ሟች የሆነ ሰው ከእንግዲህ እንዳያሸብራቸው፣+አባት ለሌለው ልጅና ለተደቆሱ ሰዎች ፍትሕ ታሰፍናለህ።+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “በነፍሱ ምኞት ይኩራራልና።”
“ስግብግብ ሰው ራሱን ይባርካል” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “ጉራውን ይነዛል።”
ወይም “ፈጽሞ አልንገዳገድም (አልውተረተርም)።”
ወይም “በጥሻው ውስጥ እንዳለ።”
ወይም “ወላጅ አልባ ለሆነው ልጅ።”