መዝሙር 82:1-8

  • የጽድቅ ፍርድ ለማግኘት የቀረበ ልመና

    • አምላክ “በአማልክት” መካከል ይፈርዳል (1)

    • ‘ለችግረኛው ተሟገቱ’ (3)

    • “እናንተ አማልክት ናችሁ” (6)

የአሳፍ+ ማህሌት። 82  አምላክ በመለኮታዊ ጉባኤ መካከል ይሰየማል፤*+በአማልክት* መካከል ይፈርዳል፦+  2  “ፍትሕ የምታዛቡት እስከ መቼ ነው?+ለክፉዎችስ የምታዳሉት እስከ መቼ ነው?+ (ሴላ)  3  ለችግረኛውና አባት ለሌለው ተሟገቱ።*+ ረዳት የሌለውና ምስኪኑ ፍትሕ እንዲያገኝ አድርጉ።+  4  ችግረኛውንና ድሃውን ታደጉ፤ከክፉዎችም እጅ አድኗቸው።”  5  ፈራጆቹ ምንም አያውቁም፤ ደግሞም አያስተውሉም፤+በጨለማ ውስጥ ይመላለሳሉ፤የምድር መሠረቶች ሁሉ ተናግተዋል።+  6  “እኔም እንዲህ አልኩ፦ ‘እናንተ አማልክት* ናችሁ፤+ሁላችሁም የልዑሉ አምላክ ልጆች ናችሁ።  7  ይሁንና እናንተም ሰው እንደሚሞተው ትሞታላችሁ፤+ደግሞም እንደ ማንኛውም ገዢ ትወድቃላችሁ!’”+  8  አምላክ ሆይ፣ ተነስ፤ በምድርም ላይ ፍረድ፤+ብሔራት ሁሉ የአንተ ናቸውና።

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “በመለኮት ጉባኤ ይሰየማል።”
ወይም “እንደ አምላክ ባሉ።”
ወይም “ፍረዱ።”
ወይም “እንደ አምላክ ያላችሁ።”