መዝሙር 6:1-10

  • ሞገስ ለማግኘት የቀረበ ልመና

    • ሙታን አምላክን አያወድሱም (5)

    • አምላክ ሞገስ ለማግኘት የሚቀርብን ልመና ይሰማል (9)

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ በሸሚኒት ቅኝት፣* በባለ አውታር መሣሪያዎች የሚታጀብ። የዳዊት ማህሌት። 6  ይሖዋ ሆይ፣ በቁጣህ አትውቀሰኝ፤በታላቅ ቁጣህም አታርመኝ።+   ይሖዋ ሆይ፣ ዝያለሁና ሞገስ አሳየኝ።* ይሖዋ ሆይ፣ አጥንቶቼ ተንቀጥቅጠዋልና ፈውሰኝ።+   አዎ፣ እጅግ ተረብሻለሁ፤*+ይሖዋ ሆይ፣ ይህ እስከ መቼ ድረስ ነው? ብዬ እጠይቅሃለሁ።+   ይሖዋ ሆይ፣ ተመለስ፤ ደግሞም ታደገኝ፤*+ለታማኝ ፍቅርህ ስትል አድነኝ።+   ሙታን አንተን አያነሱም፤*በመቃብር* ማን ያወድስሃል?+   ከመቃተቴ የተነሳ ዝያለሁ፤+ሌሊቱን ሙሉ መኝታዬን በእንባ አርሳለሁ፤*በለቅሶ አልጋዬን አጥለቀልቃለሁ።+   በሐዘኔ ምክንያት ዓይኔ ደክሟል፤+ከሚያጠቁኝ ሰዎች ሁሉ የተነሳ ዓይኔ ፈዟል።*   እናንተ መጥፎ ምግባር ያላችሁ ሁሉ ከእኔ ራቁ፤ይሖዋ የለቅሶዬን ድምፅ ይሰማልና።+   ይሖዋ ሞገስ እንዲያሳየኝ የማቀርበውን ልመና ይሰማል፤+ይሖዋ ጸሎቴን ይቀበላል። 10  ጠላቶቼ በሙሉ ያፍራሉ፤ ደግሞም እጅግ ይደነግጣሉ፤በድንገት ውርደት ተከናንበው ወደ ኋላ ያፈገፍጋሉ።+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ምሕረት አድርግልኝ።”
ወይም “ነፍሴ እጅግ ተረብሻለች።”
ወይም “ነፍሴን ታደጋት።”
ወይም “አያስታውሱም።”
ወይም “በሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ቃል በቃል “አልጋዬ እንዲዋኝ አደርጋለሁ።”
ወይም “አርጅቷል።”