መዝሙር 70:1-5

  • አፋጣኝ እርዳታ ለማግኘት የቀረበ ልመና

    • “ለእኔ ስትል ፈጥነህ እርምጃ ውሰድ” (5)

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የዳዊት መዝሙር፤ ማስታወሻ ሆኖ የሚያገለግል።* 70  አምላክ ሆይ፣ አድነኝ፤ይሖዋ ሆይ፣ እኔን ለመርዳት ፍጠን።+  2  ሕይወቴን* ለማጥፋት የሚሹኀፍረትና ውርደት ይከናነቡ። በእኔ ላይ በደረሰው ጉዳት ደስ የሚሰኙአፍረው ወደ ኋላ ይመለሱ።  3  “እሰይ! እሰይ!” የሚሉ አፍረው ወደ ኋላ ይመለሱ።  4  አንተን የሚፈልጉ ግንበአንተ ይደሰቱ፤ ሐሴትም ያድርጉ።+ የማዳን ሥራህን የሚወዱ፣ ምንጊዜም “አምላክ ታላቅ ይሁን!” ይበሉ።  5  እኔ ግን ምስኪንና ድሃ ነኝ፤+አምላክ ሆይ፣ ለእኔ ስትል ፈጥነህ እርምጃ ውሰድ።+ አንተ ረዳቴና ታዳጊዬ ነህ፤+ይሖዋ ሆይ፣ አትዘግይ።+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ለመታሰቢያ።”
ወይም “ነፍሴን።”