መዝሙር 115:1-18

  • ክብር መሰጠት ያለበት ለአምላክ ብቻ ነው

    • በድን የሆኑ ጣዖታት (4-8)

    • ምድር ለሰው ልጆች ተሰጠች (16)

    • ‘ሙታን ያህን አያወድሱም’ (17)

115  ከታማኝ ፍቅርህና ከታማኝነትህ የተነሳ+ለእኛ ሳይሆን፣ ይሖዋ ሆይ፣ ለእኛ ሳይሆን፣*ለስምህ ክብር ስጥ።+   ብሔራት “አምላካቸው የት አለ?” ለምን ይበሉ?+   አምላካችን ያለው በሰማያት ነው፤እሱ የወደደውን ሁሉ ያደርጋል።   የእነሱ ጣዖቶች ከብርና ከወርቅ የተሠሩ፣የሰው እጅ ሥራ ናቸው።+   አፍ አላቸው፤ መናገር ግን አይችሉም፤+ዓይን አላቸው፤ ማየት ግን አይችሉም፤   ጆሮ አላቸው፤ መስማት ግን አይችሉም፤አፍንጫ አላቸው፤ ማሽተት ግን አይችሉም፤   እጅ አላቸው፤ መዳሰስ ግን አይችሉም፤እግር አላቸው፤ መራመድ ግን አይችሉም፤+በጉሮሯቸው የሚያሰሙት ድምፅ የለም።+   የሚሠሯቸውም ሆኑ የሚታመኑባቸው ሁሉ፣እንደ እነሱ ይሆናሉ።+   እስራኤል ሆይ፣ በይሖዋ ታመኑ፤+እሱ ረዳታቸውና ጋሻቸው ነው።+ 10  የአሮን ቤት ሆይ፣+ በይሖዋ ታመኑ፤እሱ ረዳታቸውና ጋሻቸው ነው። 11  እናንተ ይሖዋን የምትፈሩ፣ በይሖዋ ታመኑ፤+እሱ ረዳታቸውና ጋሻቸው ነው።+ 12  ይሖዋ ያስታውሰናል፤ ደግሞም ይባርከናል፤የእስራኤልን ቤት ይባርካል፤+የአሮንን ቤት ይባርካል። 13  ይሖዋ እሱን የሚፈሩትን፣ታናናሾችንም ሆነ ታላላቆችን ይባርካል። 14  ይሖዋ እናንተን፣አዎ፣ እናንተንና ልጆቻችሁን* ያበዛል።+ 15  ሰማይንና ምድርን የሠራው+ይሖዋ ይባርካችሁ።+ 16  ሰማያት የይሖዋ ናቸው፤+ምድርን ግን ለሰው ልጆች ሰጣት።+ 17  ሙታንም ሆኑ ወደ ዝምታው ዓለም* የሚወርዱ ሁሉ፣+ያህን አያወድሱም።+ 18  እኛ ግን ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም፣ያህን እናወድሳለን። ያህን አወድሱ!*

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “የእኛ የምንለው ምንም ነገር የለም፤ ይሖዋ ሆይ፣ የእኛ የምንለው ምንም ነገር የለም።”
ቃል በቃል “ወንዶች ልጆቻችሁን።”
ቃል በቃል “ወደ ዝምታ።”
ወይም “ሃሌሉያህ!” “ያህ” የይሖዋ ስም አጭር መጠሪያ ነው።