መዝሙር 145:1-21

 • ታላቅ ንጉሥ የሆነውን አምላክ ማወደስ

  • ‘የአምላክን ታላቅነት አውጃለሁ’ (6)

  • “ይሖዋ ለሁሉም ጥሩ ነው” (9)

  • ‘ታማኝ አገልጋዮችህ ያወድሱሃል’ (10)

  • የአምላክ ዘላለማዊ ንግሥና (13)

  • ‘የሕያዋን ፍጥረታትን ሁሉ ፍላጎት ታሟላለህ’ (16)

የዳዊት የውዳሴ መዝሙር። א [አሌፍ] 145  ንጉሡ አምላኬ ሆይ፣+ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፤ለዘላለም ስምህን አወድሳለሁ።+ ב [ቤት]   ቀኑን ሙሉ አወድስሃለሁ፤+ለዘላለም ስምህን አወድሳለሁ።+ ג [ጊሜል]   ይሖዋ ታላቅ ነው፤ እጅግ ሊወደስም ይገባዋል፤+ታላቅነቱ አይመረመርም።*+ ד [ዳሌት]   ትውልዶች ሁሉ ሥራህን ያወድሳሉ፤ስላከናወንካቸው ታላላቅ ነገሮች ይናገራሉ።+ ה []   ታላቅ ውበት ስለተጎናጸፈው ግርማህ ይናገራሉ፤+እኔም ስለ ድንቅ ሥራዎችህ አሰላስላለሁ። ו [ዋው]   እጅግ አስደናቂ ስለሆነው ሥራህ* ይናገራሉ፤እኔም ስለ ታላቅነትህ አውጃለሁ። ז [ዛየን]   የጥሩነትህን ብዛት ሲያስታውሱ በስሜት ያወራሉ፤+ከጽድቅህም የተነሳ እልል ይላሉ።+ ח [ኼት]   ይሖዋ ሩኅሩኅና* መሐሪ፣+እንዲሁም ለቁጣ የዘገየ ነው፤ ታማኝ ፍቅሩም ታላቅ ነው።+ ט [ቴት]   ይሖዋ ለሁሉም ጥሩ ነው፤+ምሕረቱም በሥራው ሁሉ ላይ ይታያል። י [ዮድ] 10  ይሖዋ ሆይ፣ ሥራዎችህ ሁሉ ከፍ ከፍ ያደርጉሃል፤+ታማኝ አገልጋዮችህም ያወድሱሃል።+ כ [ካፍ] 11  የንግሥናህን ክብር ያውጃሉ፤+ስለ ኃያልነትህም ይናገራሉ፤+ ל [ላሜድ] 12  ይህም ለሰዎች ታላላቅ ሥራዎችህንና+የንግሥናህን ታላቅ ክብር+ ያስታውቁ ዘንድ ነው። מ [ሜም] 13  ንግሥናህ ዘላለማዊ ነው፤ግዛትህም ከትውልድ እስከ ትውልድ ጸንቶ ይኖራል።+ ס [ሳሜኽ] 14  ይሖዋ ሊወድቁ የተቃረቡትን ሁሉ ይደግፋል፤+ያጎነበሱትንም ሁሉ ቀና ያደርጋል።+ ע [አይን] 15  ዓይን ሁሉ አንተን በተስፋ ይመለከታል፤አንተም ምግባቸውን በወቅቱ ትሰጣቸዋለህ።+ פ [] 16  አንተ እጅህን ትዘረጋለህ፤የሕያዋን ፍጥረታትንም ሁሉ ፍላጎት ታሟላለህ።+ צ [ጻዴ] 17  ይሖዋ በመንገዱ ሁሉ ጻድቅ፣+በሥራውም ሁሉ ታማኝ ነው።+ ק [ኮፍ] 18  ይሖዋ ለሚጠሩት ሁሉ፣በእውነት* ለሚጠሩት+ ሁሉ ቅርብ ነው።+ ר [ረሽ] 19  የሚፈሩትን ሰዎች ፍላጎት ያረካል፤+እርዳታ ለማግኘት የሚያሰሙትንም ጩኸት ይሰማል፤ ደግሞም ይታደጋቸዋል።+ ש [ሺን] 20  ይሖዋ የሚወዱትን ሁሉ ይጠብቃል፤+ክፉዎችን ሁሉ ግን ይደመስሳል።+ ת [ታው] 21  አፌ የይሖዋን ውዳሴ ያስታውቃል፤+ሕያዋን ፍጥረታት በሙሉ ቅዱስ ስሙን* ለዘላለም ያወድሱ።+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ከመረዳት ችሎታ በላይ ነው።”
ወይም “ኃይልህ።”
ወይም “ቸርና።”
ወይም “በቅንነት።”
ቃል በቃል “ሥጋ ሁሉ ቅዱስ ስሙን።”