መዝሙር 24:1-10

  • ክብር የተጎናጸፈው ንጉሥ

    • ‘ምድር የይሖዋ ናት’ (1)

የዳዊት መዝሙር። ማህሌት። 24  ምድርና በውስጧ ያለው ነገር ሁሉ፣ፍሬያማ የሆነችው ምድርና በእሷ ላይ የሚኖር ሁሉ የይሖዋ ነው።+   እሱ በባሕሮች ላይ መሥርቷታልና፤+በወንዞችም ላይ አጽንቶ አስቀምጧታል።   ወደ ይሖዋ ተራራ መውጣት የሚችል ማን ነው?+በቅዱስ ስፍራውስ ሊቆም የሚችል ማን ነው?   ከክፋት የጸዱ እጆችና ንጹሕ ልብ ያለው፣+በእኔ ሕይወት* በሐሰት ያልማለ፣በማታለልም መሐላ ያልፈጸመ።+   እሱ በረከትን ከይሖዋ ያገኛል፤+ጽድቅንም* አዳኝ ከሆነው አምላኩ ይቀበላል።+   እሱን የሚፈልጉ ሰዎች ትውልድ ይህ ነው፤የያዕቆብ አምላክ ሆይ፣ ፊትህን የሚፈልጉ ሰዎች ትውልድ እንዲህ ያለ ነው። (ሴላ)   እናንተ ደጆች፣ ራሳችሁን ቀና አድርጉ፤+እናንተ ጥንታዊ በሮች፣ክብር የተጎናጸፈው ንጉሥ ይገባ ዘንድ ተከፈቱ!*+   ይህ ክብር የተጎናጸፈ ንጉሥ ማን ነው? ብርቱና ኃያል የሆነው ይሖዋ ነው፤+በውጊያ ኃያል የሆነው ይሖዋ ነው።+   እናንተ ደጆች፣ ራሳችሁን ቀና አድርጉ፤+እናንተ ጥንታዊ በሮች፣ክብር የተጎናጸፈው ንጉሥ ይገባ ዘንድ ተከፈቱ! 10  ይህ ክብር የተጎናጸፈ ንጉሥ ማን ነው? የሠራዊት አምላክ ይሖዋ ነው፤ ክብር የተጎናጸፈው ንጉሥ እሱ ነው።+ (ሴላ)

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “በነፍሴ።” አንድ ሰው የሚምልበትን የይሖዋን ሕይወት ያመለክታል።
ወይም “ፍትሕንም።”
ወይም “ከፍ በሉ።”